በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂሪንግ ኢንዱስትሪ በእስቶክ ውስጥ የሚገኙትን ያለቀለትና በከፊል ያላለቀለት ምርቶችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለጅምላ አከፋፋዮች መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂሪንግ ኢንዱስትሪ በእስቶክ ውስጥ የሚገኙትን ያለቀለትና በከፊል ያላለቀለት ምርቶችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለጅምላ አከፋፋዮች መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 12, 2026)

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር መኢኢግ/ኤኢኢ/001

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂሪንግ ኢንዱስትሪ በእስቶክ ውስጥ የሚገኙትን ያለቀለትና በከፊል ያላለቀለት ምርቶችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለጅምላ አከፋፋዮች መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ በአክብሮት ተጋብዟችኋል።

ተቁ

Name of goods

Lot

Bank Guarantee

1

Power Factor Correction(PFC) Intelligent Module & Accessories

01

1,803,425.99

2

Energy Meter Accessories And Components

02

2,826,534.00

 

Grand Total

 

4,629,960

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ሎት ወይም ለሁሉም ሎቶች ለብቻው በፖስታ አሽገው ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል በመሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው።

6. በተጫራቾች የሚያቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።

7. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ በኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ከግብይትና ሽያጭ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለገጣፎ ቅሪንጫፍ በኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ አካውንት ቁጥር 1000692062144 ገቢ በማድረግ ሰነዱን መውሰድ ትችላላችሁ።

8. ተጫራቾች የጨረታ የሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት አየር ላይ ውሎ 16ኛው ቀን ከቀኑ 830 ይዘጋል። በዚሁ ዕለትም ከቀኑ 900 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪያችን በዲዛይን አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

10. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።

11. ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾችም ይህን አውቀው የዋስትና ጊዜው ጨረታው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለው የባንክ ዋስትና ማረጋገጥ አለባቸው።

12. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም። ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

13. አድራሻ፡ሸገር ከተማ ኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ 44 ማዞሪያ ለገዳዲ ውሃ ማጣሪያ ግድብ አጠገብ ነው።

ለበለ መረጃ፡በስልክ ቁጥራችን 09 24 24 97 48 / 09 10 40 88 33 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *