በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የባዶ ኮንቴነር ማመላለሻ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የባዶ ኮንቴነር ማመላለሻ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 12, 2026)

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ESLSE/P&T/REQ/2025/02712

በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ለኤክስፖርት የሚያገለግሉ ባዶ ኮንቴነሮችን ለማስጫን ስለፈለገ የሀገር ውስጥ የጭነት ትራንስፖርት አክሲዎን ማህበራትን በማወዳደር ካሸናፊው ማህበር ጋር ውል በማሰር ማሠራት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተቀመጡትንመስፈርቶች የሚያሟሉ ማህበራትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

ሎት-አስር፡ የባዶ ኮንቴነር ማመላለሻ አገልግሎት ግዥ

በዚህም መሰረት፡-

  1. በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት የምስክር ወረቀት የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ ሥልጣን ካለው አካል የተሰጠ ማስረጃ (Valid tax clearance)፤
  3. የታደሰ ሶስተኛ ወገን እና ኢንሹራንስ ሰነድ ማቅረብ የሚችል።
  4. ከትራንስፖርት ባለሥልጣን የተሰጠ የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ከነ ሰሌዳ ቁጥር ወይንም የተሽከርካሪዎችን የባለቤትነት ደብተር (ሊብሬ) ዝርዝር ማቅረብ የሚችል።
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር) በንግድ ባንክ፣ በህብረት ባንክ ወይንም በኦሮሚያ ህ/ሥራ ባንክ ብቻ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርበታል።
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ የሚመልሰው በድርጅቱ ድረ-ገጽ (WWW.ESLSE.COM)ላይ በERP SYSTEM በዋና መ/ቤት ምዝገባ ካካሄዱ በኋላ ብቻ (ከዚህ ቀደም ያልተመዘገቡ ከሆነ) በሚሰጣቸው መለያ  ቁጥር መሰረት የሚሞሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
  7. የጨረታው መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜ ሲስተሙ ላይ በሚወጣው ሰዓት ይሆናል
  8. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0221162194 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ

የሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *