በጌዲኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አጥር እና የመጸዳጃ ቤት በዘርፉ የተሰማሩትን ማኅበራትን በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በጌዲኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አጥር እና የመጸዳጃ ቤት በዘርፉ የተሰማሩትን ማኅበራትን በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 12, 2026)

የግንባታ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጌዴኦ ዞን ባህላዊ መልከዓ ምድር ዓለም ዓቀፍ ቅርስ አስተዳደር ጽ/ቤት ከፌዴራል ቅርስ ባለስልጣን ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በይርጋ ጨፌ ወረዳ ጨልባ ቱቲቲ ትክል ድንጋይ አጥር እና የመጸዳጃ ቤት በዘርፉ የተሰማሩትን ማኅበራትን በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።

ስለዚህ በመስኩ የተሠማራችሁ ተጫራቾ

  • በደረጃ 8 የተደራጁ ማኅበራት፤
  • የዘመኑን ግብር የከፈለና የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያለውና ማቅረብ የሚችል፤
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  • በከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር የተመዘገቡና የታደሰ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  • የ2017 በጀት ዓመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ከገቢዎች የተሰጠ ሰርተፍኬት የሚያቀርብ፤
  • በክልሉ እና በዞናችን ውስጥ በግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው ሥራዎችን ያላስተጓጎሉ ውል ያላቋረጡ መሆን ይገባቸዋል፤
  • የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይረክቶሬት ዘውትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመውስድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ የጨረታ ሰነድ እያንዳንዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ እንድ ላይ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት በ16ኛው ቀን ይሆናል።
  • ኦርጅናል ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ በሚታይ መልኩ በድጋሚ መጻፍ አለበት።
  • በእያንዳንዱ የጨረታ ስነድ ላይ የማኅበሩ ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት።
  • ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ እየር ላይ ለ15 ተከታታይ ቀን ከዋለበት በኋላ በ16ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
  • ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 120,000 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና ከታወቀባንክ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ለ90(60+30)ቀን የሚቆይ በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ እና በኢንሹራንስ ዋስትና መቅረብ አይቻልም፣
  • ጨረታው የሚገመገመው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት እንደገና ተሻሽሎ በወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 70/2017 እና በዚሁ መመሪያ ላይ ማብራሪያና ማሻሻያ በተደረገው መሠረት ነው።
  • በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደርጋል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁፕር 046 131 0108 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
በጌዲኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *