Be'kur (May 11, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የባህር ዳር ከተማ አስተዳዳር ማረሚያ ቤት መምሪያ ለህግ ታራሚዎች ለምግብነት የሚዉሉ የተለያዩ በሎት የተገለጹ ግብአቶችን መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም
- ሎት1 ፡-የባልትና ውጤት
- ሎት፡-2 የፋብሪካ ዉጤት፤ እንቁላል
- ሎት፡-3 የማገዶ እንጨት
- ሎት፡4 ፊኖዱቄት
- ሎት፡-5 አትክልት
- ሎት፡-6 የቅባት እህል
- ሎት፡-7 ጤፍ እና በቆሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ
ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፍርቶች ማሟላት የምትችሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡-
- በዘርፍ ህጋዊ ፈቀድ ያላቸዉና ከመንግስት ሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ ለመሆናቸዉ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ከ200 ሺህ ብር በላይ ሽያጭ ለሚፈፅሙ አቅራቢዎች ቫት ከማይጠየቅባቸዉ ዉጭ ባሉት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸዉ ማስረጃ የሚያቀርቡ።
- ተጫራቾች በስራ ፋቃዳቸዉ መሰረት መቅረብ የሚገባቸዉን ለይተዉ በመሙላት በታሸገ ፓስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ዉስጥ ከጫራታ መክፈቻዉ ቀንና ሰአት በፊት ማስገባት አለባቸዉ።
- ተጫራቾች ለመወዳደር ባቀረቡባቸዉ የምግብ ግብዓቶች የገንዘብ መጠን ልክ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1 100,000 ብር ሎት2 100,000 ብር ሎት3 100,000 ብር ሎት4 50,000 ብር ሎት5 5,000 ብር ሎት6 1,500 ብር ሎት7 150,000 ብር በባንክ በተመሰከረለት CPO፣ በጥሬ ገንዘብ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረበ አለባቸው። አሸናፊዉ ዉል ሲይዝ የዉል ማስከበሪያ በጨረታ ማስከበሪያ ላይ ገንዘብ በመጨመር የሚያስዝ ሆኖ ለተሽነፈ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ይሆናል።
- ከ20 ሺህ ብር በላይ ለሆነ ሽያጭና የሽያጭ ታክስ ከሚከፈለዉ ጠቅላላ ገንዘብ ላይ በመመሪያዉ መሰረት 3 በመቶ መክፋል ይኖርበታል።
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ በመለየትና በተለያዩ ፖስታ በማሽግ ሰነዱ ላይ ፊርማ እና የድርጅታችዉን ማህተም ማሳረፍ አለባቸዉ።
- የጨረታ አሸናፊዎች ዉጤቱ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋዉን 10 በመቶ በማስያዝ ዉል ይዘዉ ያሸነፋባቸዉን ባ/ዳር ማረሚያ ቤት መምሪያ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታዉ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በ16ኛዉ ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል። መምሪያው ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 058-320-3139 ደውለው ወይም በአካል ባ/ዳር ማረ/ቤት መምሪያ ግዥ/ፋን/ንብ/አስ/ስራሂደት በመምጣት መጠየቅ ይቻላል።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳዳር ማረሚያ ቤት