Be'kur (May 11, 2026)
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. የተለያየ መጠን ያላቸው BUTTWELDING HDPE PIPE፣
- ሎት 2. Flanged Water Meter፣
- ሎት 3. Submersible pump እና
- ሎት 4. የሂሳብ ምርመራ (የኦዲት) አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ወይም የታደሰ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናል፣ ኮፒውን፣ ፋይናሻል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር ለየብቻ በማሸግና ሁሉንም በአንድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሎት 4 ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ማስያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያዉ ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያዉ ሰነድ ካለበት ፖስታ ዉስጥ አስገብቶ በዋናው ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
7. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል።
8. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ጽ/ቤቱ በመቅረብ 10በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ እና ውል በመፈፀም እቃውን ባ/ዳር ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 05 83 20 50 79 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
11. አድራሻ ቀበሌ 08 ዋናው የባሕር ዳር ከተማ የመ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት።
የባህር ዳር ከ/የመ /ው/ፍ/አገ/ድርጅት