Addis Zemen (May 12, 2026)
ጊዜያዊ ካምፕ ግንባታ ለማከናወን የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/14/2018
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን ልዩ ቦታው ማጂ ኮካ እየሰራ ላላው የኮኮ እርሻ ልማት ጊዜያዊ የሰራተኞች መኖሪያ የቢሮ፤ የጋራዥ የመመገቢያ አዳራሽ እና ማብሰያ ኪችን፤ የመፀዳጃ ቤት እና የመጋዘን ግንባታ ማከናወን ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ደረጃ 7 (ሰባት) እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወይም ደረጃ 6 (ስድስት) እና ከዚያ በላይ የህንፃ ሥራ ተቋራጭ ፤ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ፡ ቲን፤ ቫት ተመዘጋቢነት ሰርተፊኬት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ EGP (የአቅራቢ ተመዝጋቢነት)።እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ አ.ማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ _ ወይም በባንከ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ዋጋ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል። ጨረታው ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል። ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡–
ስልክ +251911984467 ወይም +251910567578
ፋክስ 0114-421312
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ