Addis Zemen (May 13, 2026)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሣሽ ፀደይ ባንክ (የቀድሞው አብቁተ አረርቲ ቅ/ጽ/ቤት) እና በአፈ/ተከሣሾች እነ በላቸው አንዱአለምና ጓደኞቻቸው የታክሲ አገልግሎት ህብረት ሽርክና ማህበር (11ሰዎች) መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈጻጸም ተከሣሽ ንብረት የሆኑት ባጃጆች፡–
1/ የሰሌዳ ቁጥሩ አማ 1-32672፣ የሞተር ቁጥሩAK4AJ44929570፣ የሻንሲ ቁጥር WAYACARWAJG006721፣
2/ የሰሌዳ ቁጥሩ አማ 1-32674፣ የሞተር ቁጥሩ AK4AJ4225905፣ የሻንሲ ቁጥር WAYACAHWAJG006625
3/ የሰሌዳ ቁጥሩ አማ 1-32675፣ የሞተር ቁጥሩ AK4A4429492 የሻንሲ ቁጥር WAYACARWAJG006715
የሆኑትን እያንዳንዳቸው በመነሻ ዋጋ በብር 263,461 /ሁለት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ አራት መቶ ስልሳ አንድ ብር/ በአረርቲ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ግቢ ተሽከርካሪዎቹ በቆሙበት ሰኔ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በተራ ቁጥር 1ኛ እና 2ኛ የተጠቀሱት ባጃጆች ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በተራ ቁጥር 3 የተጠቀሰው ባጃጅ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል።
በመሆኑም፡–
1. ተጫራቾች ያሸነፉበትን 1/4ኛውን በሲፒኦ ወዲያውኑ ለሀራጅ ባዩ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው።
2. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
3. ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው ለፍርድ ማስፈፀሚያ ነው።
4. ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሣይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል፣ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሃራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል።
5. የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል።
የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ደ/ብርሃን