Addis Zemen (May 23, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ት/ቤታችን ስኩል ኦፍ ሪደምሽን አ.ማ. ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሥራዎች በሚያቀርበው ናሙና መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል.
1.የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ዓመታዊ የኦዲት ሥራ
2. የት/ቤት ወላጅ ግንኙነት መጽሐፍ
3. የተማሪዎች የደንብ ልብስ (uniform)
4. የጥበቃና የጽዳት ሠራተኛ ልብስ እንዲሁም የሠራተኛ ሸሚዝ
5. የቅድመ አንደኛ ደረጃ (KG) ተማሪዎች መመረቂያ መጽሔት
በመሆኑም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin no.) ያላችሁ እና በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ የማይመለስ 1,000 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ለቡ ሙዚቃ ቤት በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት በመምጣት ሰነዱን በመግዛት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል. ጨረታው አየር ላይ በዋለበት በ8ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ9ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ – አዲስ አበባ ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ለቡ ሙዚቃ ሰፈር
ስ.ቁጥር፡- 0906-96-94-96/ 0938-11-88-22
ስኩል ኦፍ ሪደምሽን አ.ማ.