Addis Zemen (May 24, 2026)
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- መልካዲዳ/ስተአ/002/2018
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መልካዲዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን
- የተለያዩ ዕቃዎች
- (ላፕቶፕ እና ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፐሪንተሮች፣ የማባዣ ማሽኖች፣
- ቴሌቪዝኖች፣
- የተለያዩ የዉሃ እቃዎች፣
- የግንባታ እቃዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ በድጋሚ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መልካዲዳ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መልካዲዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከግንቦት 17/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 28/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንከ ዋስትና /Bank Gurantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 28/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መልካዲዳ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ መልካዲዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት/መጎብኘት ይችላል።
- ጨረታው መልካዲዳ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ መልካዲዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ግንቦት 28 ከቀኑ 8፡30 ታሽጎ በዕለቱ ግንቦት 28 ከቀኑ 9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።
- በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበርያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251912487328 ወይም +251912189068 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መልካዲዳ
ቅርንጫፍ ጽ/ቤት