መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ (መኢኢግ) ኤሌክትሪካል ተሽከርካሪ ግዢ፣ የጭነት ትራንስፖርት፣ የፎርክ ሊፍት እና የክሬን ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ (መኢኢግ) ኤሌክትሪካል ተሽከርካሪ ግዢ፣ የጭነት ትራንስፖርት፣ የፎርክ ሊፍት እና የክሬን ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 28, 2026)

የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ መኢኢግ/ግጨተሽ/02/2018፣ መኢኢግ/ግጨት/04/2018

1. የግዥ ፈፃሚው ስም:- መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ/መኢኢግ/

2. የግዥው ዓይነት:

  • ሎት አንድ ፡- የኤሌክትሪካል ተሽከርካሪ ግዢ 
  • ሎት ሁለት ፦ የጭነት ትራንስፖርት፣ የፎርክ ሊፍት፣ የክሬን ተሽከርካሪ ኪራይ

3. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፣ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN Number) እና በኢፌዴሪ የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢነት ኦን ላይን የተመዘገበ ና የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።

4. የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ፡- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ በአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 102 እና 105 ሀይሌ ጋርመንት የቀድሞ ሪቬራ ሆቴል ማግኘት ይችላሉ።

 5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን፡- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በእያንዳንዱ ሎት የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተወሰነ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Performance bond) ተጫራቹ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% (10 ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ሲያቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያው ይለቀቅለታል። የአሸናፊ መግለጫ

7. የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የሚከፈል የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በገንዘብ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይቻላል።

8. የመወዳደሪያው ሰነድ የሚቀርበው ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል፣ ፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል የድርጅታችሁ ማህተም የተመታበት፣ ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ የቅጂ ብዛት ለእያንዳንዱ ሰነድ አንዳንድ ኮፒ ሆኖ ሰነዶቹ ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸውና የድርጅቱ ማህተም ያለባቸው መሆን አለባቸው። እንዲሁም ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዕቃዎች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል መግለጫ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በግልጽ ከላይ በሚታይ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ብለው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

10. ጨረታው ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ፡- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በ13 ( አስራ ሶስት ) ቀናት ከጠዋት 2፡30 እስከ 10፡30 የስራ መውጫ ባሉት ሰዓቶች ሲሆን ጨረታው የሚዘጋው በቀን ማክሰኞ ቀን 02 ሰኔ 2018 ከጠዋት 4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያኑ ማክሰኞ ቀን 02 ሰኔ 2018 ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ይከፈታል።

11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን ስፔስፊኬሽንም ሆነ የዕቃ ዓይነት ከሌለው የለንም ወይም ሰረዝ(–) ማድረግ እንጂ በአማራጭ መሙላት አይችልም።

12. ግሩፑ በጨረታ ሰነዱ በሎት አንድ ላይ የተቀመጠውን የተሽከርካሪ ዝርዝር ፍላት በተጨማሪ በምስል መቅረብ ይችላል።

13. ግሩፑ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ ሲፈልጉ፡
ስልክ ቁጥር፡ 0967 26 16 36/0996117472
አድራሻ፡- ሀይሌ ጋርመንት የቀድም ሪቬራ ሆቴል አዲስ አባባ ፣ኢትዮጵያ
መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ/መኢኢግ/


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *