Addis Zemen (May 31, 2026)
የኦዲት ስራ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ስማርት ዲጂታል ቴክኖሎጂስ አ.ማ በ ኢትዮ ቴሌኮም በሃገር አቀፍ ደረጃ የቴሌኮም ምርቶችን በማከፋፈል እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡
በዚህም መሰረት ድርጅታችን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የድርጅታችን ሂሳብ በተመሰከረለት የውጪ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
በዋናው ኦዲተር የተመዘገበ ሆኖ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የታክስ መለያ ቁጥርና የሙያ ማረጋገጫ ያለው/ያላት
የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
ከፌዴራል ወይም ክልል ኦዲት መስሪያ ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፍቃድ ያለው/ያላት
በመሆኑም ሂሳቡን ለመመርመር የሚጠይቀውን የገንዘብ መጠን(ቫትን ጨምሮ) እና ስራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጀውን ጊዜ በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀመሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የተጠየቁትን ማስረጃዎች የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በማያያዝ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ በስራ ሰዓት ገቢ በማድረግ ማመልከት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡
ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
አድራሻ ቦሌ ኦሮሚያ ህንፃ 2ኛ ፎቅ (ቢሮ ቁጥር 205)
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር፡- 0924156865 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ስማርት ዲጂታል ቴክኖሎጂስ አ.ማ