አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (May 31, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ . ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸዉንና በሰንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም .. በአቢሲንያ ባንክ (.) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.. ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት .. ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።

የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ክስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።

ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።

በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ ባንኩ ከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል።

የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ /ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ ኢማ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ B 4 ፎቅ ፎርክሎዠር እና ዴት ሊትጌሽን ለጨረታ ባዘጋጀዉ ቢሮ ላይ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 . በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የተበዳሪው ስም

የመያዣ ሰጪው ስም

የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት

የቦታው ስፋት በካ.ሜ

የባለቤትነት ማረጋገጫ

ካርታ ቁጥር

ንብረቱ ቦሚገኝበት አድራሻ

የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

የምዝገባ

ሰዓት

 

የጨረታ ሰዓት

 

ጨረታ የወጣበት ጊዜ

ኢኮቶፒያ ሪሳይክሊንግ ኢንዱስትሪስ /የተ/የግ/ማህበር

ተበዳሪዉ

የኢንዱስትሪ ህንፃ

 

6000

 

EMMLMG/1/004/2006

 

ኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ሸገር ከተማ ገላን /ከተማ

65,167,932.51

 

ሰኔ 24 ቀን

2018 ዓ.ም

 

8:30-9:30

9:30-10:00

 

ለመጀመሪያ

ጊዜ

 

አቶ ተማም ዘይኑ ሁሴን

ተበዳሪዉ

የመኖሪያ ቤት

63.44 (ከአጠቃላይ ይዞታው ላይ 3.73% ወደፊት ለመንገድ ማስፋፊያ የሚቀነስ

የምስክር ወረቀት ቁጥር ETH0001000000-00004254469 የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000090707791

 

አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ /ከተማ ወረዳ 7

 

5,629,085.86

 

ሰኔ 25 ቀን

2018 .

 

4:30-5:30

5:30-6:00

 

በድጋሚ

 

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *