Addis Zemen (Jun 05, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 10/2018
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ከህጋዊ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች
1. ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ
2. ባለ 3 እግር ተሸከርካሪ
3. ብትን ጨርቅ
4. የተሰፉ ልብሶች
5. የወንድ እና ሴት ጫማ
6. ልብስ ስፌት
በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላል።
1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገቡ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ ከሆኑ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
3. ለጨረታ ዋስትና ከሚቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ፣ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት / በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ፣
4. ድርጅቱ በሚያቀርበው ስፔስፊኬሽንና ናሙና መሰረት ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት ደ/ማ/ከተማ ውሃ አገልግሎት አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን የተለያየ ፓስታ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ደ/ማ/ከ/ውሃ/አገ/አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ማስገባት ይኖርባቸዋል። በሰም አለመታሸጉ ከጨረታ ውጭ አያስደርግም።
7. በ15ኛው ቀን የጨረታ ሳጥን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሸጋል። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይከፈታል 16ኛው ቀን እሁድ ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 3፡00 ሰዓት ይከፈታል።
8. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በማጓጓዝ ደ/ማ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ስቶር ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል የማጓጓዣውንም ሆነ የሠራተኛ ጉልበት ዋጋ መ/ቤቱ አይሸፍንም።
9. ተጫራቾች የሚፈፅሟቸው ሌሎች ግዴታዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ እና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የተጫራቾች የግዥ መመሪያ ላይ በተቀመጠው አግባብ ይሆናል።
10. ድርጅቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ /መንገድ/ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ።
አድራሻ ፡– ደ/ማ/ከ/የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 058 771 6840፣ 058 771 1058፣ 058 771 1520
ማሳሰቢያ፡–
1. ቧንቧ፤ ሸሚዝ እና ብትን ጨርቅ ድርጅቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ ያለባችሁ በመሆኑ ዋጋ ከመሙላታችሁ በፊት ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት የእቃ ናሙናውን እንድታዩ እያሳሰብን፣ የእቃውን ፎቶ ግራፍ አይታችሁ ዋጋ የምትሞሉ ፎቶ የእቃን አይነት እንጅ የእቃ ጥራትን ስለማያሳይ በአካል መታችሁ ናሙናውን እንድታዩ እናስታውቃለን።
2. ርክክብ የሚፈፀመው ከተቀመጠው ናሙና ጋር አንድ አይነት መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት