የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Jun 10, 2026)

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።

ተቁ

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

የመያዣ ንብረቱ መለያ

የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር)

ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት

 

የሰሌዳ ቁጥር

ሞተር ቁጥር

የሻንሲ ቁጥር

የንብረቱ አይነት

የሥሪት ዘመን

1

ሪሳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ

ወንድም ፈለቀ

AA-02- C33705

G4LANM147995

MALB241C8

NM149028

ሃዩንዳይ ግራንድ i10 አዉቶሞቢል

2022

3,098,304.00

 

17/10/2018  3:00-4:00 ጠዋት

2

አቶ ናስር ካሊል ሞሐመድ

ተበዳሪው

02-AA-B76699

JFC92432.

 

1FTEX1EP1 JFC92432 

ፎርድ የ150 ኪንግ ካፕ

2018

 

4,765,200,00

 

17/10/2018 ዓ.ም 4፡00-500 ጠዋት

 

3

ኳድራንት አፓርል ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ተበዳሪው

ኢት-03-66900 እና ኢት-03-20264

F3BEE681G *B220222647*

 

WjME3TRE8 EC286633 እና TT-1044-14

የጭነት እና ተሳቢ ተሽከርካሪ

 

2014

11,033,376.00

 

17/10/2018ዓ.ም 5፡00-6፡00 ጠዋት

 

 በመሆኑም፡-

1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።

2. ጨረታዉ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ነዉ።

3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።

4. ለጨረታ የቀረበውን ንብረት በጨረታ አሸንፎ የገዛ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል።

5. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።

6. ንብረቱን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል።

7. በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

8. ንብረቱን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም᎓᎓ ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቱን ካልተረከበ ከንብረቱ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

9. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-13-05-08 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሕግ ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *