ማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም በ2018 ዓ.ም. ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮችን፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን እና በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ ሞተር ብስክሌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም በ2018 ዓ.ም. ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮችን፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን እና በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ ሞተር ብስክሌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 28, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም በ2018 ዓ.ም. ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮችን፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን እና በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ ሞተር ብስክሌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች መሳተፍ ይችላሉ፡-

1. በዘርፍ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀትና ቫት የተመዘገቡበት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡

2. ከፋይናንስና ኢ/ል/ቢሮ የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋገጥ የምዝገባ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ በየዘርፉ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ CPO ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብቻ በመክፈል ከማርጯ/አ/የፋ/ተቋም ፋይናንስና በጀት መምሪያ ድረስ በመቅረብ ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማርጯ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም ስም በተከፈተው ቁጥር 1000564691252 ገንዘብ ገቢ በማድረግ ያስገቡበትን የባንክ አድቫይሱን በ E-mail: marchuwa23@gmail.com  በመላክ በስልክ ቁጥር 0949616937 ደውለው በመግለጽ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ መ/ቤቱ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. የጨረታ ሣጥን ጋዜጣው ከወጣበት አሥር /10/ ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡15 ሰዓት በቢሮ ይከፈታል፡፡

7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046 180 76-66 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *