ብርሃን ባንክ አ.ማ. የመኖሪያ እና ንግድ ቤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ብርሃን ባንክ አ.ማ. የመኖሪያ እና ንግድ ቤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Jun 28, 2026)

የሐራጅ ማስታወቂያ

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ከባለእዳዎቹ ላይ ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረትቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል።

1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን የ1/4 (አንድ አራተኛ) (ሲፒኦ) በብርሃን ባንክ ኢማ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

2. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን እንዳሸነፈ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ አለበት። በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።

3. የመኖሪያ ንግድ ቤቶቹ ጨረታ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ይከናወናል።

4. የጨረታ አሸናፊው በሚገዛው ንብረት ላይ የሚፈለግ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያዎች እና የሊዝ ክፍያዎች ይመለከተዋል።

5. መያዣ ሰጪዎች ሐራጁ በሚከናወንበት ቦታ ቀንና ሰዓት መገኘት ይችላሉ:: ባይገኙ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።

6. በባንኩ ብድር መምሪያ መስፈርት መሰረት እና በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የሚፈለግበትን ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል።

7. ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ኘሮግራም አስይዞ ለመጐብኘት ይቻላል።

8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

የመኖሪያ እና ንግድ ቤቶች

.

 

የተበዳሪዉ ስም

 

የመያዣ ሰጭዉ ስም

መኖሪያ/ የንግድ ቤት የሚገኝበት አድራሻ

የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር

የንብረቱ አገልግሎት

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

የጨረታ መነሻ ዋጋ

ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት፤

1

አብርሃም መንግስቱ

 

የማነህ ከበደ

 

ገላን ከተማ 01 ቀበሌ የቤት ቁጥር አዲስ

400 .(G+1)

 

መኖሪያ ቤት

 

BMG/20/2002

 

8,100,000.00

 

ሐምሌ 21 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400-530

 

2

ይርጋለም ፀጋዬ

 

ሞርኒንግ ስታር ማቀነባበሪያ /የተ/ የግ/ማህበር

 

ደብረ ብርሃን ከተማ ጠባሴ /ከተማ ሸፍኑ ቀበሌ

10085.34 .

 

ኢንዱስትሪ

 

ደብኢፓ/03/0033/2014

 

41,200,000.00

 

ሐምሌ 22 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400-530

 

3

እርሳሱ እመን

 

እርሳሱ እመን

 

አርባ ምንጭ ከተማ አሬንቻ ቀበሌ

250 .

 

መኖሪያ ቤት

 

1592/15

 

2,400,000.00

 

ሐምሌ 22 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400-530

4

ዮሴፍ አበበ

 

ዮሴፍ አበበ

አለታ ወንዶ ከተማ መሳለሚያ ቀበሌ

327.77 .

 

መኖሪያ ቤት

 

SD011020102018

 

1,850,000.00

 

ሐምሌ 23 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400-530

5

ትብቃ ፈነታ

 

ትብቃ ፈነታ

 

ብቸና ከተማ 01 ቀበሌ

250 .

 

ድርጅት

ብቸ0.2461/11

 

4,150,000.00

 

ሐምሌ 23 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400-530

6

ደረጄ ካሳሁን

 

ቢያይልኝ ወርቅነህ

 

ፍኖተ ሰላም ከተማ 02 ቀበሌ

150 .

 

መኖሪያ ቤት

6187/2014

 

1,600,000.00

 

ሐምሌ 24 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400-530

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 011-650 6900 እና 011-650 6276 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *