የሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ የ2016፣ 2017 እና የ2018 ሂሳብ ከGAAP ወደ IFRS የተዘጋጀውን conversion መርምሮ የሚያረጋግጥ ኦዲተር በጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ የ2016፣ 2017 እና የ2018 ሂሳብ ከGAAP ወደ IFRS የተዘጋጀውን conversion መርምሮ የሚያረጋግጥ ኦዲተር በጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 30, 2026)

የውጪ ኦዲት አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ የ2016፣2017 እና የ2018 ሂሳብ ከGAAP ወደ IFRS የተዘጋጀውን conversion መርምሮ የሚያረጋግጥ ኦዲተር በጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

1. በዘርፉ የታደስ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡-

2. በጨረታ ማስከበሪያነት የሚወዳደሩበትን ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይገባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ለዚህ ግዥ የተዘጋጀውን ተ.ኦ.አር ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ባሉት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከድርጅታችን ግዥ ንብ/ጠ/አገ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 05 ቀርበው በነጻ መውሰድ ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በኢንተርፕራይዛችን በግዥ ንብ/ጠ/አገ ዳይሬክቶሬት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ላይ ታሽጎ ወዲያውኑ በ9፡00 የሚከፈት ይሆናል፡ ዘግይተው የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ጊዜ የሚከፈት ይሆናል፡፡

6. የኢንተርፕራይዛችን አድራሻ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት አካባቢ የክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ባለበት ጊቢ ውስጥ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462123472 ወይም 0912005137 መደወል ይችላሉ።

የሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *