Addis Zemen (Jun 30, 2026)
የኦዲት ሥራ ባለሙያ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጡረተኞች ማህበር ከሐምሌ 01 ቀን 2017 ዓ.ም. በጀት ዓመት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ተከታታይ የበጀት ዓመታት ሂሳቡን ለማስመርመር (ኦዲት ለማስደረግ) ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ የኦዲት ተቋማት አወዳድሮ አሸናፊውን መምረጥ ይፈልጋል።
መሟላት የሚገባቸው መሥፈርቶች
- በአዋጅ ቁጥር 847/2006 አንቀጽ18 መሠረት የኦዲት ሙያ ማረጋገጫ ያለውና በመንግሥት የተመዘገበ፣
- በኦዲት ሥራ በቂ ልምድ ያለው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣
- ከአሁን በፊት ኦዲት ያደረጋቸውን ድርጅቶች ዝርዝር ማቅረብ የሚችል፣
ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) የስራ ቀናት ውስጥ የምትሰሩበትን ዋጋ እና ሥራውን ሠርታችሁ የምታቀርቡበትን ጊዜ በመጥቀስ ደረጃችሁን እና ሕጋዊነታችሁን የሚገልጽ ማስረጃዎቻችሁን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ በማመልከት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናው መስሪያ ቤት ግቢ ውስጥ ነው።
የስልክ ቁጥር፡- 011 517-8283 /011 517-8753 ሞባይል፣ 09 37-92-96-03
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጡረተኞች ማህበር