ፀሐይ ባንክ አ.ማ. የተለያዩ ንበረቶችን በግልጽ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ፀሐይ ባንክ አ.ማ. የተለያዩ ንበረቶችን በግልጽ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Jun 28, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ፀሐይ ባንክ አ.ማ. ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ቀጥሎ ባለው ሠንጠረዥ ውስጥ የተመለከተውን ንብረት/ሕንጻ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በአዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንብረቱ ባሉበት ሁኔታና አሁን በሚገኙበት ይዞታ ላይ እንዳለ በግልጽ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

.

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

የአበዳሪው ቅርንጫ

የንብረቱ አድራሻ

የቦታ ስፋት

የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር

የንብረቱ ዓይነት/የይዞታ አገልግሎት

የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር

ጨረታው የሚካሄድበት

የተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት

የጨረታው ደረጃ

 

ክልል

 ከተማ

ክፍለ ከተማ/ወረዳ/ቀበሌ

ቀን

ሰዓት

1

አቶ አእምሮ ሙሉዬ ምህረቴ

 

አቶ አእምሮ ሙሉዬ ምህረቴ

 

አያት 72

አማራ

ባህር ዳር ከተማ

አፄ ቴውድሮስ ክፍለ ከተማ/ ማራኪ ቀበሌ

150 .

11/2112/2013

የመኖሪያ ቤት G+2

13,608,703.32

ሐምሌ 23 ቀን 2018.

400 እስከ 600 ሰዓት

400 እስከ 530 ሰዓት

ለመጀመሪያ ጊዜ

 

2

አዲናስ /የተ/የግ/ማህበር

አዲናስ /የተ/የግ/ማህበር

 

በቅሎ ቤት

አማራ

ባህርዳር ከተማ

ጣና /ከተማ/ቀበሌ 16

5,000 .

ባህኢፓ/0154/2011

ለፋብሪካ የሚያገለግል ሕንጻ/መጋዘን

42,237,204.74

ሐምሌ 23 ቀን 2018.

800 እስከ 1000 ሰአት

800 እስከ 930 ሰዓት

ለመጀመሪያ ጊዜ

 

ኢንጁክሲ ትሬዲንግ /የተ/የግ/ማህበር

በቅሎ ቤት

አማራ

ቲሊሊ ከተማ

ጓሽ ወረዳ/ጅባይታ ቀበሌ

 

 

10,000 .

ጓሽ/01/11

ለፋብሪካ የሚያገለግል ሕንጻ/መጋዘን

7,366,180.08

ሐምሌ 24 ቀን 2018.

400 እስከ 600 ሰአት

400 እስከ 530 ሰዓት

ለመጀመሪያ ጊዜ

 

ማሳሰቢያ፦ በሐራጁ(ጨረታ) መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ(CPO) ብቻ በፀሐይ ባንክ አ.ማ. (Tsehay Bank S.C.) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  2. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝጊያ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ እስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል፡፡ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በባንኩ የሚመለከተው የስራ ክፍል ፀድቆ የጨረታ አሸናፊ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲሰጠው ብቻ ነው።
  3. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ ሕግ መምሪያ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤ በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለጨረታ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ክፍያ ማዘዣ(CPO) ይመለስላቸዋል።
  4. ንብረቱን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘብ ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቱን ካልተረከበ ከንብረቱ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
  5. የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ማናቸውንም ክፍያዎችን፣ የሊዝ ክፍያ፤ ግብር፣ በሽያጩ ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ይከፍላል፡፡ በተ.ቁ 1 ላይ የተገለጸው የመኖሪያ ቤት የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% ታሳቢ አይደረግበትም።
  6. በተ.ቁ 2 ላይ የተገለጹት ሁለቱም ፋብሪካዎች ሐራጁ የሚመለከተው የፋብሪካውን ሕንጻዎች ብቻ ሲሆን በውስጡ ሊኖር የሚችል ሌላ ማናቸውንም አይነት ንብረት አያካትትም።
  7. ለሐራጅ ጨረታ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች በስራ ሰዓት በአካል በመምጣት ወይም ጨረታው ከሚደረግበት 5 ቀን በፊት ሕግ አገልግሎት መምሪያ ወይም ባሕር ዳር ዲስትሪክት ስልክ በመደወል እና ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ።
  8. ባንኩ ስመንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው የመንግስት አካል ተገቢውን የድጋፍ ደብዳቤ ይጽፋል።
  9. የጨረታው ቦታ ባሕር ዳር ከተማ ጣና ክፍለ ከተማ በተለምዶ ኖክ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ድባንቄ የገበያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የባንኩ የባሕር ዳር ዲስትሪክት የሚደረግ ይሆናል።
  10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የሐራጁ መሰረዝ ለባንኩ ጥቅም ሲባል ሐራጁ ተካሂዶ ከፍተኛ የጨረታ ዋጋ አቅራቢ ከታወቀ በኋላም ሊሆን ይችላል።
  11. በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም የእነዚህ ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡ በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ አካል ከሆነ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት ዋና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ቲን ሰርተፊኬት፣ እንዲሁም ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ጽ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የጸደቀ የድርጅቱ መመስረቻ ፅሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፤ቃለ ጉባዔ ወይም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት፡፡ ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል።
  12. ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም ህጋዊ ተወካዮች የጨረታውን ሒደት ለመከታተል ከላይ በተጠቀሰው ቦታና ቀን እንድትገኙ እያሳሰብን ካልተገኛችሁ በሌላችሁበት ጨረታው የሚከናወን መሆኑን እንገልጻለን።
  13.  በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ሕጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅቶችም ያገለግላል።

ለበለጠ መረጃ ፀሐይ ባንክ አ.ማ. ሕግ አገልግሎት መምሪያ +0114704915 ወይም +0114705354 ወይም +0583206746 መደወል ይቻላሉ።
ፀሐይ ባንክ ለሁሉ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *