Be'kur (Jun 29, 2026)
የመሬት ሊዝ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ዙር 3ኛ/2018 ዓ.ም
ጨረታው አይነት /መደበኛ
1. የሻሁራ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም ለመኖሪያና ለድርጅት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መጫረት የሚፈልጉ ሁሉ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከሰኔ 22/2018 እስከ ሐምሌ 3/2018 ዓ.ም የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፍል ሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 27 ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከሰኔ 22/2018 እስከ ሐምሌ 3/2018 ዓ.ም ነው፡፡
3. ጨረታው የሚዘጋው ሐምሌ 3/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ይሆናል፡፡
4. ቦታውን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ሰኔ 27፣29 እና ሐምሌ 02 መጎብኘት ይችላሉ፡፡
5. ጨረታው የሚከፈተው ሐምሌ 3/2018 ከረፋዱ 3፡00 በሻሁራ ከተማ አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
6. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የማራዘም እና ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
7. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 32 75 06 77 ወይም 09 18 13 81 73 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሻሁራ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የመሬት ሊዝ ጨረታ የቦታዎች ዝርዝር መረጃ
|
ተ.ቁ |
አገልግሎት |
የሚገኝበት ቀጠና |
የሚገኝበት ቀበሌ |
ብሎክ ቁጥር |
ፕሎት ቁጥር |
ስፋት በካ.ሜ |
መነሻ ዋጋ |
ጠቅላላ ዋጋ |
የግንባታው ደረጃ |
|
1 |
መኖሪያ |
ቴዎድሮስ |
02 |
108 |
ጨመ-04 |
150 |
500 |
75,000 |
G+0 |
|
2 |
መኖሪያ |
ቴዎድሮስ |
02 |
108 |
ጨመ-03 |
150 |
500 |
75,000 |
G+0 |
|
3 |
መኖሪያ |
አንድነት |
01 |
104 |
ጨመ– 973 |
150 |
500 |
75,000 |
G+0 |
|
4 |
መኖሪያ |
አንድነት |
01 |
104 |
ጨመ– 972 |
150 |
500 |
75,000 |
G+0 |
|
5 |
መኖሪያ |
አንድነት |
01 |
104 |
ጨመ– 971 |
150 |
500 |
75,000 |
G+0 |
|
6 |
ድርጅት |
አንድነት |
01 |
107 |
ጨድ-01 |
300 |
800 |
240,000 |
G+4 |
|
7 |
ድርጅት |
አንድነት |
01 |
107 |
ጨድ-02 |
300 |
800 |
240,000 |
G+4 |
መግለጫ
- ጨድ፡- ለጨረታ የቀረበ የድረጅት ቦታ ማለት ነው፡፡
- ጨመ- ለጨረታየቀረበ የመኖሪያ ቦታ ማለት ነው፡፡
የሻሁራ ከተማ አስ/መሬት ጽ/ቤት