በአብክመ የኦሮ/ብ/ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ ለተለያዩ መኪናዎች መለዋወጫዎች፣ በኪሎሜትር የሚቀየሩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የሞተር ሳይክል ጎማዎች፣ ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ጌጣጌጦች እና የመኪና ዘይትና ቅባቶች በአንድ ዓመት የሚቆይ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ በሎት ዋጋ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአብክመ የኦሮ/ብ/ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ ለተለያዩ መኪናዎች መለዋወጫዎች፣ በኪሎሜትር የሚቀየሩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የሞተር ሳይክል ጎማዎች፣ ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ጌጣጌጦች እና የመኪና ዘይትና ቅባቶች በአንድ ዓመት የሚቆይ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ በሎት ዋጋ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jul 11, 2026)

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የኦሮ/ብ/ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኘው ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል በ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ ለተለያዩ መኪናዎች መለዋጫዎች፣ በኪሎሜትር የሚቀየሩ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የሞተር ሳይክል ጎማዎች፣ በአንድ ዓመት የሚቆይ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ በሎት ዋጋ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ መስፈርቶቹም፦

  1. የተለያዩ የመኪና ጎማዎች
  2. የሞተር ሳይክል ጎማዎች፣
  3. የመኪና መለዋወጫዎች
  4. በኪሎሜትር የሚቀየሩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች
  5. ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ጌጣጌጦች
  6. የመኪና ዘይትና ቅባቶች

7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ጨረታ ማለትም በተራ ቁጥር 1 ለተገለጸው 75.000/ሰባ, አምስት ሺህ ብር/ ለተራ ቁጥር-2 /30000/ሰላሳ ሺህ/ ብር ለተራ ቁጥር-3 /100000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ለተራ ቁጥር-4 /50000/ ሃምሳ ሺህ ብር/ ለተራ ቁጥር-5 /30000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ለተራ ቁጥር 6 /50000/ ሃምሳ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በገቢ መቀበያ ደረሰኝ በኦሮሞ/ብ/ዞን/በደ/ጨ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በምርጫቸው በአንዱ ከዋናው ኦሪጅናል የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. በዘርሩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።

9. ተጫራቾች የምዝገባ የምስክር ወረቀት (Tin No) አብረው ማያያዝ የሚችሉና

10. ከ 200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

11. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የያዘ ከኦሮ/ብ/ዞ/ደ/ጨ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ለ15 አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ገዝተው በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ |ኤንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

12. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን 4:30 የሚከፈት መሆኑን አየገለጽን፣ ሆኖም የመክፈቻው ዕለት ባኣላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

13. ተጫራቾች ለሞሉት ለጠቅላላ የጨረታ መጠን ላይ 1% /ፐርሰንት/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

14. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት መረጃ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ለበለጠ መረጃ የተጫራቾችን መመሪያ ላይ መረዳት ይቻላል; ወይም በስልክ ቁጥር- 033-554-1794 መደወልና መጠየቅ ይችላሉ።

15. አሸናፊዎች ያሸነፉትን እቃ ደዋ ጨፋ ወረዳ ገን/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። በጨረታ አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች ውል ካልገቡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ በሙሉ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

16. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በአብከመ የኦሮ/ብ/ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *