Reporter (Jul 19, 2026)
የሐበሻ ቢራ አ.ማ ምርቶች አከፋፋይነት ማስታወቂያ
1. መግቢያ
ሐበሻ ቢራ አ.ማ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ቀዳሚ የመጠጥ አምራቾች ውስጥ አንደኛው ሲሆን እ.ኤ.አ በ2009 በሺዎች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች ከኔዘርላንዱ የመጠጥ አምራች ሮያል ስዊንክልስ ጋር በመሆን ኢትዮጵያዊ የሆነና በመላ ሃገሪቱ የሚገኘውን ማኅበረሰብ የሚያስተሳስር ምርት ለማቅረብ የተመሰረተ ነው። ፋብሪካው እ.ኤ.አ በ2015 የማከፋፈል ሥራውን የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅትት ንጉስ ማልት፥ ፈታ ቢራ፡ ቅዳሜ ቢራ እና በዋናነት የሚታወቅበትን ሐበሻ ቢራን በማከፋፈል በኢትዮጵያ ውስጥ ቀዳሚ ከሚባሉት መጠጦች አምራቾች ውስጥ መመደብ ችሏል። ፋብሪካው ከአዲስ አበባ በ130 ኪሜ ርቀት በምትገኘው ደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኝ ሲሆን ምርቶቹንም ከፋብሪካው ወደ መላው የሀገሪቱ ክፍል እያከፋፈለ ይገኛል።
ሐበሻ ቢራ በሚከተሉት ከተሞች እና አካባቢዎች ብቁ የሆኑ አከፋፋዮችን መድቦ ማሠራት ይፈልጋል
|
ቦታ/ከተማ/አካባቢ |
|
ቦንጋ፥ ውሽውሽ፥ ዲሪ፥ ሺንሺዳ |
|
ዲማ እና አካባቢው |
|
ጋምቤላ ከተማ እና አካባቢው |
|
ጊንቢ፥ ነጆ፥ መንዲ |
|
በደሌ፥ ያዩ |
|
ነቀምት፣ ጉቲን |
|
ጂማ፥ አጋሮ፥ ሱንቱ፥ ሶኮሩ |
|
ደብረ ታቦር፥ አዲስ ዘመን፥ ወረታ፥ እስቴ፥ እብናት፥ ንፋስ መውጫ |
|
ደብረ ማርቆስ፥ ሉማሜ፥ አማኑኤል፥ ኤሊያስ፥ ደምበጫ |
|
ፍኖተ ሰላም፥ ቡሬ |
|
ጎንደር ከተማ |
|
ጎንደር (ማክሰኚት፥ እንፍራንዝ፥ ጎርጎራ፥ ደልጊ፥ ሻውራ) |
|
ሰመራ፣ ሎጊያ፥ ሚሌ፥ አዳይቱ |
|
አቢይ አዲ፥ ይቺላይ፥ ሃገረ ሰላም፥ ወርቅኣምባ |
|
ቱላ፥ ለኩ፥ ይርጋአለም፡ ጪኮ፥ አለታ ወንዶ፥ ሀገረ ሰላም |
|
መተሃራ፥ አዋሽ አርባ፥ መይሶ፥ ገዋኔ |
2. አከፋፋዩ እንዲያሟላ የሚጠበቁ መስፈርቶች 1
- ደረጃዉን የጠበቀ ፥ በቂ ምርት ማከማቸት የሚያስችል እንዲሁም የሐበሻ ቢራን የምርት ማከማቻ መጋዘን ደረጃ የሚያማላ መጋዘን በሚሰራበት የሽያጭ ክልል ውስጥ ያለው ያላት
- የበር ለበር ሽያጭን ለማከናወን የሚያስችል ዝቅተኛ ሁለት ኤን ፒአር/ኤፍ ኤስ አር መኪኖችን ማቅረብ የሚችል፥ የመኪናዉ ብዛት የገበያውን አቅም መሰረት በማድረግ ከፍ እንዲል ሊደረግ ይችላል
- ለስራው የሚጠየቀውን ዝቅተኛ የስራ ካፒታል አስር ሚሊየን ብር ማቅረብ የሚችል፥ የገንዘብ መጠኑ የገበያውን አቅም መሰረት በማድረግ ከፍ እንዲል ሊደረግ ይችላል
- ምርት በራሱ ከፋብሪካ መውሰድ የሚችል ቢሆን ያመረጣል
- የሺያጭ፥ የመጋዘን እና ሌሎች ስራዎችን ለመከወን የሚያስችል በቂ የሰው ሃይ ማቅረብ የሚችል
- ከዚህ በፊት ምርት የማከፋፈል ልምድ ያለው ያላት ቢሆን ይመረጣል
- ስላመለከተበት ገበያ በቂ እውቀት ያለው፥ የአካባቢው ቋንቋ የሚችል፣ ከማህበረሰቡ ጋር ጥሩ ግንኙነት ያለው እና የአካባቢውን ባህልና የደንበኞች ባህሪ ጠንቅቆ የሚያውቅ
3. ለማመልከት የሚያስፈልጉ ሰነዶች
- የቢራና ከአልኮል ነጻ ምርቶች አከፋፋይነት ንግድ ፈቃድ፣ ዋና ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢነት ማረጋገጫ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማረጋገጫ፣ እና የታክስ ከሊራንስ ምስክር ወረቀት በቅድሚያ ማሟላት የሚችል/ የምትችል
- የቀበሌ መታወቂያ/ የቢዝነሱ ባለቤት ፋይዳ
- ለቢዝነሱ የሚውል የባንክ ሂሳብ የ6 ወር የሂሳብ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሰነድ
- የድርጅቱን የቢዝነስ ታሪክ፥ የማከፋፈል አቅም እና አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች መረጃዎችን የሚያሳይ የድርጅት ሰነድ
- የመጋዘን እና ተሽከርካሪዎች ባለቤት መሆኑን የሚያሳይ ወይንም ተከራይቶ ከሆነ የኪራይ ውሉ ሰነዶች
- የተሽከርካሪዎች መረጃ ብዛት እንዲሁም አይነትና የመጫን አቅም
4. ማሳሰብያ
- ይህ ማስታወቂያ ማንኛውም አይነት የህግም ሆነ የውል ግንኙነት ከሐበሻ ቢራ ፋብሪካ ጋር አይፈጥርም።
- ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ ኢማ ማስታወቂያውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝም ሆነ የማሻሻል መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማመልከቻውን አለማስገባት የጨረታ ማመልከቻው ውድቅ እንዲደረግ ሊያደርግ ይችላል።
- ወደ ቀጣይ ዙር ያለፉ እጩዎችን በጠቀሱት የስራ ቦታ ላይ ጉብኝት ይደረጋል።
አመላካቾች በ6977 የሐበሻ የጥሪ ማዕከልን በመጠቀም ተጨማሪ መረጃ እና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ።
ማመልከቻው በታሸገ ፖስታ ውስጥ ሆነ በግልጽ በሚታይ መልኩ የድርጅቱ ስም እንዲሁም የማመልከቻው ምክንያት የተጻፈበት መሆን አለበት (፦ ለአከፋፋይነት ፍላጎት መግለጫ)
ፍላጎት ያላቸው እና ብቁ የሆኑ አመልካቾች የፍላጎት መግለጫውን ከሰነዶቹ ኮፒ ጋር አያይዘው ቦሌ አየር መንገድ ካርጎ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐበሻ ቢራ ዋና መስሪያ ቤት ግራዉንድ ፍሎር በአካል በመቅረብ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማመልከት ይኖርባቸዋል።
ሐበሻ ቢራ አ.ማ