የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማዎችን፣ ባጃጅና ሞተር ሳይክሎችን፣ ለኤሌክትሪክና ለውሃ ዝርጋታ የሚያገለግሉ እቃዎች፣ ለቴክንክና ሙያ ኮሌጅ ሥልጠና የሚያገለግሉ እቃዎችን እና የደንብ ልብሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማዎችን፣ ባጃጅና ሞተር ሳይክሎችን፣ ለኤሌክትሪክና ለውሃ ዝርጋታ የሚያገለግሉ እቃዎች፣ ለቴክንክና ሙያ ኮሌጅ ሥልጠና የሚያገለግሉ እቃዎችን እና የደንብ ልብሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jul 19, 2026)

የጨረታ ስታወቂያ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ /ቤት በከተማው መስተዳድር ስር ለሚገኙ ሴክተር /ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ፡

  1. የፅህፈት መሳሪያዎች
  2. የፅዳት እቃዎች
  3. የኤሌክትሮንክስ እቃዎች
  4. ቋሚ የቢሮ እቃዎች
  5. ያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማዎችን
  6. ባጃጅና ሞተር ሳይክሎችን
  7. ኤሌክትሪክና ውሃ ዝርጋታ የሚያገለግሉ እቃዎች
  8. ለቴክንክና ሙያ ኮሌጅ ሥልጠና የሚያገለግሉ እቃዎችን
  9. የደንብ ልብሶችን

በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ማጠናቀቁንና፣ ጨረታ ላይ እንድሳተፍ የሚል ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን /ቤት ማቅረብ አለበት።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN No.) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው።
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ከፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 3000.00( ሦስት ሺህ ብር) በመክፈል ከሞጆ ከተማ ገንዘብ /ቤት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል።
  7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ CPO ብር 60,000.00(ስልሳ ሺህ ብር) ሲሆን ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ የትኛውንም የዋስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
  8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ፎቶኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል።
  10. ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው የስራ ቀን 400 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሞጆ ከተማ ገንዘብ//ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም /ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
  11. አሽናፊው ያሸነፈበትን የእቃ አይነት አሸናፊ መሆኑን ካወቀበት ቀን ጀምሮ 10 ቀን ውስጥ የእቃውን ናሙና ማቅረብ አለበት።
  12. የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እስከ ሞጆ ከተማ ገንዘብ /ቤት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዘው ማቅረብ አለባቸው።
  13. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያና በስልክ እንደተገለፀ 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ከሞጆ ከተማ ገንዘብ /ቤት ጋር መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ይሆናል።
  14. አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለጸለት ያሸነፈበትን እቃ ብዛት አባዝቶ የጠቅላላውን ዋጋ 10% የውል ዋስትና ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ለሞጆ ከተማ ገንዘብ /ቤት ብሎ በመፃፍ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  15. መስሪያ ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ መገንዘብ አለበት።
  16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

መረጃ፡

ቁጥር፡-0221161644/2239 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ /ቤት