Addis Zemen (Jul 21, 2026)
ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የደብረብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል ለተሽከርካሪዎች የኢንሹራንስ አገልግሎት በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ብር 200000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT)ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የአገልግሎት ግዥ ፍላጎት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር)በማዕከሉ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመቅረብና በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ)ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ ብር)በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ(CPO)ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በደብረብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል ስም በመክፈል የተከፈለበትን ደረሰኝ ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሽገው በደብረ ብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል በግዥ ባለሙያዎች ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በመቁጠር በተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ይህ ማስታወቂያ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በመቁጠር በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ ይከፈታል።
- በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች የአገልግሎት ግዥውን ተጫራቾች በደ/ብርሃን ከተማ የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቅርንጫፍ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- የግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደብረብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0116736918 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
የደብረብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል