በአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎቶች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎቶች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Jul 20, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት

  • ሎት 1. የህክምና ኦክስጅን ግዥ፣
  • ሎት 2 የሰራተኞች ማመላለሻ የመኪና ሰርቪስ አገ/ት ግዥ፣
  • ሎት 3 የጽዳት አገ/ት ግዥ
  • ሎት፣ 4 የደረቅ ጭነት መኪና ኪራይ አገ/ት ግዥ እንዲሁም
  •  ሎት 5 የሆስፒታሉ ጣራ ቀለም ቅብ፣ ባዞላ ንጣፍ እና ኮንቲነር ግንባታ ደረጃ 6 እና በላይ የሆኑ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
  1.  ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ካርድ ሰርተፊኬት እና ከመንግስት የሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ ማስረጃ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ በሎት 3 ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች አንድ አመት እና በላይ የሆነ በዘርፉ የብቃት ማረጋገጫ ልምድ ከመንግስት ተቋማት እንዲሁ በሎት 5 ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3.  የግዥዉ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5.  ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3 መዉሰድ የሚቻል ሲሆን ጨረታዉ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ቀን ድረስ እስከ 11፡30 ብቻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በልዩ ልዩ ምክንያት በሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ያልታገዱ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በአማርኛ ቋንቋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር ያካተተ ሆኖ የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ የድርጅቱ ክብ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ ማስቀመጥ አለባቸዉ፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ ማድረግ የለባቸዉም፡፡ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ማንኛዉንም የመንግስት ግብር አካቶ የሞሉትን ጠቅላላ ድምር አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከፖስታው ውስጥ አብሮ ማስገባት አለባቸዉ፡፡ በሎት 4 ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች ግን በብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) ብቻ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  9.  ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸዉ ከታወቀ ማንኛዉንም የመንግስት ግብር አካቶ የሞሉትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ በሎት 4 ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች ግን 20,000 (ሀያ ሽህ ብር ) ብቻ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙ ግን ፕሮግራሙ የማይስተጓጎል ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ 058 827 04 27 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል