የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለስልጤ ዞን አስተዳደር እንግዳ ማረፊያ የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ለማሰራት በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለስልጤ ዞን አስተዳደር እንግዳ ማረፊያ የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ለማሰራት በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jul 21, 2026)

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለስልጤ ዞን አስተዳደር እንግዳ ማረፊያ የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ለማሰራት በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ደረጃቸው B.C/G.C-6 እና ከዛ በላይ የሆኑ፤ ሎት2. የመጸዳጃ ቤት ግንባታ

  • የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ
  • የታደሰ የንግድ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስተር የዘመኑን የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፤
  • የጨረታ ዋስትና 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ፤
  • የመስራት አቅም እንዳላቸው የሚገልፅ የወቅቱን የባንክ እስቴትመንት እና የስራ ልምድ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የኦዲት ሪፖርት እና የድርጅቱን አወቃቀርና ከዚህ በፊት የሰሯቸውን ስራዎች የሚገልፅ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮች ሰነድ ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነድን ፋይናንሻል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናል እና 2ኮፒ ለየብቻ፣ ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከቀኑ 800 ሰዓት ድረስ ስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ 20ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 830 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 20ኛው ቀን የስራ ቀን ከልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡

ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ።

የተወዳዳሪ ተቋራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለወጡም።

 መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡ስልክ ቁጥር 046 771 0586 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

በማዕ/// የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *