Addis Zemen (Jul 23, 2026)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎች በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ማለትም፡–
- ሎት 1 የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት2 የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች
- ሎት3 የተለያዩ ፈርኒቸሮች
- ሎት4 የተለያዩ ሞተሮች
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑ ግብር በመክፈል ፍቃድ ያደሳችሁ እና ፍቃዳቹ ኦንላይን የተመዘገባቹ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ማቅረብ የሚችሉ።
- በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተወዳዳሪዎች ለወረዳችን 7.50% ገቢ የምታደርጉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ገንዘብ ለሎት1. 20,000 (ሀያ ሺህ)፣ ለሎት2 20,000(ሀያ ሺህ) ለሎት3 20,000(ሀያ ሺህ) እና ለሎት4 20,000 (ሀያ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠለት ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆነባቸው እቃዎች እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አጠቃላይ በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱን ሎት የጨረታው ዝርዝር የያዘ ዶክመንት ለመግዛት የሚያስችል የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00ሰዓት ድረስ ሰነዳቸው ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/ከ/ን/አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸውን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበርያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ መስርያ ቤቱ የጨረታ ማስከበርያውን የመውረስ መብት አለው።
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማለትም ቅዳሜና እሁድ እዲሁም የበዓል ቀናት ጨምሮ አየር ላይ ይውላል:: ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ15 ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገርግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የተጫረቱባቸው እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
ማሳሰቢያ፡– ሰነዱ ማግኘት የሚቻለው ተወዳዳሪው በአካል ወይንም ህጋዊ ለሆነ አካል ብቻ ነው።
ወረዳው በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 197 ኪ.ሜ ላይ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ 09-23-13 37-39 እና 09-23-51 95-14
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን
እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት /አገና/