Reporter (Jul 26, 2026)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ ደሳለዉ ወርቁ ረዴ ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዛቸዉንና ዝርዝር ሁኔታቸዉ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪ ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
የንብረቱ መገኛ፤ ደረጃና ካርታ ቁጥር |
የጨረታዉ መነሻ ዋጋ |
|
1 |
ለአቶ ደሳለዉ ወርቁ ረዴ |
ለአቶ ደሳለዉ ወርቁ ረዴ |
ፍኖተ ሰላም ከተማ ቀበሌ 02 ካርታ ቁጥር 471-14-2014 መኖሪያ ቤት 200 ካ/ሜ |
6,712,996.89 |
|
2 |
ለአቶ ደሳለዉ ወርቁ ረዴ |
ለአቶ ደሳለዉ ወርቁ ረዴ |
አዉቶሞቢል ቻይና ቮልስዋገን ID6-CROZZ የሰሌዳ ቁጥር AA-02-C28536 chanssis ቁጥር LFVVB9E70 N5160926 |
5,119,010.4 |
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል::
1. ተጫራቾች የቤቱን/የተሸከርካሪዉን የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1/4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
2. የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጨረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል::
3. በጨረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ድርጅት ከሆነ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት::
4. የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨራታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል::
5. በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸመል::
6. የጨረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ/ ተሸከርካሪዉ ጋር የተያያዙ ማንኛዉንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ወጭዎችን ገዢ ይከፍላል:: ማንኛዉም ዉዝፍ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር ዉል እንዲዋዋል ይደረጋል::
7. ተጫራቾች ቤቱን እና ተሸከርካሪዉን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ::
8. ጨረታዉ የሚካሄደዉ ነሃሴ 20/2018 ከጠዋቱ ከ3-5 የተጫራቾች ምዝገባ፣ ከ5 እስከ 6 ሰዓት ጨረታ በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክ/ከተማ ልዩ ቦታዉ ሰንጋ ተራ በባንኩ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ይሆናል::
9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
ለተጨማሪ መረጃ፡– ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት በስ.ቁ +251 115 582 978 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል::