የቦሌ ሚካኤል ኮንዶሚኒየም ኃላፊነቱ የተወሰነ የቤት ባለቤቶች ኅብረት ሥራ ማህበር ሒሳብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የቦሌ ሚካኤል ኮንዶሚኒየም ኃላፊነቱ የተወሰነ የቤት ባለቤቶች ኅብረት ሥራ ማህበር ሒሳብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 07, 2026)

የሒሳብ ባለሙያ ጨረታ ማስታወቂያ

የቦሌ ሚካኤል ኮንዶሚኒየም ኃላፊነቱ የተወሰነ የቤት ባለቤቶች ኅብረት ሥራ ማህበር ከሐምሌ 01 ቀን 2008 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ያለውን የገቢ ደረሰኞች 593 ፓዶች (አምስት መቶ ዘጠና ሶስት ፓዶች እና የወጪ ደረሰኞች 9 ፓዶች (ዘጠኝ ፓዶች) በድምሩ 602 ፓዶች (ስድስት መቶ ሁለት) ፓዶችን ሒሳብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም በዘርፉ የተሰማራችሁ ባለሙያዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  • የታደሰ የሒሳብ ስራ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
  • ቫት ከፋይ የሆነች እና ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል የምትችል
  • የሒሳብ መሞከሪያ /trial balance/፣ የገቢ (እና) የወጪ /income Statement/፣ የሀብት እና እዳ መግለጫ Balance Sheet/ ሰርቶ በመጨረሻም የተገኘውን ግኝት በተጨባጭ ማስረጃ በማያያዝ የሚያቀርብ የምታቀርብ
  • ሒሳቡ ካለቀ በኋላ ለኦዲተሮች የሰራውን ስራ ማስረዳት የሚችል የምትችል በመሆኑም መወዳደር የምትፈልጉ ዋጋችሁን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለተከታታይ 10 ቀናት ማለትም እስከ 10/12/2018 ዓ/ም ድረስ በስራ ሰዓት በማህበሩ ጽ/ቤት ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
  • ጨረታው የሚያበቃበት በ11/12/2018 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት መሆኑን እናሳውቃለን።
  • ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ- ቦሌ ሚካኤል ኮንደሚኒየም/ቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር- 09 11 41 80 22/ 09 31 41 89 89 ይደውሉ።
የቦሌ ሚካኤል ኮንዶሚኒየም ኃላፊነቱ የተወሰነ የቤት ባለቤቶች ኅብረት ሥራ ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *