ሠንጋተራ አንድነት ትሬዲንግ አ.ማ. ለሚቀጥሉት ሶስት ተከታታይ አመታት ማለትም 2019፣ 2020 እና 2021 የበጀት አመታት የሂሳብ መዛግብቱንና የፋይናንስ መግለጫዎቹን መርምሮ ሪፖርት የሚያቀርብለት ብቁ የውጪ ኦዲት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ሠንጋተራ አንድነት ትሬዲንግ አ.ማ. ለሚቀጥሉት ሶስት ተከታታይ አመታት ማለትም 2019፣ 2020 እና 2021 የበጀት አመታት የሂሳብ መዛግብቱንና የፋይናንስ መግለጫዎቹን መርምሮ ሪፖርት የሚያቀርብለት ብቁ የውጪ ኦዲት ይፈልጋል


Reporter (Aug 12, 2026)

የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

(Invitation for External Audit Service)

ድርጅታችን ሠንጋተራ አንድነት ትሬዲንግ አ.ማ. ለሚቀጥሉት ሶስት ተከታታይ አመታት ማለትም 2019 2020 እና 2021 የበጀት አመታት የሂሳብ መዛግብቱንና የፋይናንስ መግለጫዎቹን መርምሮ ሪፖርት የሚያቀርብለት ብቁ የውጪ ኦዲት ይፈልጋል። አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት አወዳድሮ መቅጠር

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ የውጪ የኦዲት አገልግሎት የሚሰጡ ማህበራት ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፦

1. ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡

1.1.ለበጀት ዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ

1.2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማረጋገጫ ሰርተፊኬት።

1.3. ከሂሳብና ኦዲት ቦርድ (AABE) ወይም ከፌዴራል ኦዲተር ዋና መስሪያ ቤት የተሰጠ የታደሰ የሙያ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት።

1.4. ተመሳሳይ ድርጅቶች ወይም ማህበራት የኦዲት አገልግሎት የሰጡበት የተረጋገጠ ልምድ።

1.5. የድርጅቱ መግለጫ (Company Profile) በኦዲት ስራው የሚሰማሩ ባለሙያዎችን ዝርዝር እና የትምህርት ዝግጅት /የስራ ልምድ።

2. የጨረታ አቀራረብ ሁኔታ፡

2.1. ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሠነዶቻቸውን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት አገልግሎት የሚሰጡበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ በፊት ወይም ከተጨማሪ እሴት በኋላ /VAT/ መሆኑን በግልጽ በማሳወቅ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2.2. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዳቸውን በማህበሩ /ቤት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

2.3. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

2.4. አድራሻ፡ ሠንጋተራ ነጋዴዎች ሕብረት ሕንፃ አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4FA-026

ስልክ ቁጥር፡ +251 92 014 2164

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *