የመልካ ጀብዱ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2019 ዓ.ም ለመምህራንና ለአስተዳደር ሰራተኞች ከድሬዳዋ መልካ ጀብዱ ትምህርት ቤት የትራንስፖርት ሰርቪስ ለመስጠት በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የመልካ ጀብዱ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2019 ዓ.ም ለመምህራንና ለአስተዳደር ሰራተኞች ከድሬዳዋ መልካ ጀብዱ ትምህርት ቤት የትራንስፖርት ሰርቪስ ለመስጠት በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል


Melekite Dire (Aug 05, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የመልካ ጀብዱ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2019 ዓ.ም ለመምህራንና ለአስተዳደር ሰራተኞች ከድሬዳዋ መልካ ጀብዱ ትምህርት ቤት የትራንስፖርት ሰርቪስ ለመስጠት በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

የተጫራቾች መመሪያ

  1. የዘመኑ የመንግስት ግብር የከፈለበት ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  2. የታደሰ መንጃ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል።
  3. ተሸከርካሪው ከ45 በላይ የሰው ሀይል መያዝ የሚችል።
  4. ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የተሸከርካሪ የደረጃ ፍቃድ ያለው።
  5. ተጫራቾች በዋጋ የሚቀርብ ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. የሶስተኛ ወገን ዋስትና መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ 10.000 (አስር ሺ ብር) በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማሲያዝ ይኖርበታል፡፡
  8. ጨረታው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት) ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብና ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
  9. የጨረታው ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ከሐምሌ 29/2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት የተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የጨረታው ሳጥን ነሐሴ 14/2018 ከጥዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያኑ በ4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  11.  የሰርቪስ መኪና ቢበላሽ ያለምንም ምክኒያት ወዲያውኑ ተለዋጭ መኪና መተካት የሚችል።
  12. ትምህርት ቤቱ በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት ሰርቪስ አገልግሎት መስጠት የሚችል።
  13. መኪናውን ለመገምገም እንዲያቀርብ ሲጠየቅ ወዲያውኑ ማቅረብ የሚችል።
  14. ውሉ ከመስከረም 4/2019 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም ይሆናል።
  15. ትምህርት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. አሸናፊው ድርጅት ለከፍያ የሚያቀርበው ደረሰኝ የማህበሩ ህጋዊ ደረሰኝ መሆን አለበት።

ይህ የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ።

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0920687625


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *