Addis Zemen (Aug 13, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በጋሞ ዞን የቦረዳ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ እና በካፒታል በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች ከሎት1 – ሎት 5 ከታች በዝርዝር የተቀመጡ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. ጽ/መሳሪያ (የቢሮ አላቂ ዕቃዎች የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች)
- ሎት 2.ኤሌክትሮኒክስ (ኮምፒውተር ፣ፕሪንተር ፣ ኮፒ ማሽን እና ተዛማች ዕቃዎች)
- ሎት 3.ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል
- ሎት 4. የግንባታ ዕቃዎች
- ሎት 5. የሰራተኛ ደንብ ልብስ
የተጫራቾች መስፈርት ፦
1/ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀትያለው፤
2/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤
3/ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀትያለው፤ የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
4) የጨረታ ማስከበሪያ /BID BOND/ ለእያንዳንዱ ሎት /40,000.00/አርባ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከቴክኒካል ኦርጂናል ጨረታ ሠነድጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት።
5/ የተጫረቱትን ዕቃ እስከ ወረዳው ፋ/ፕ/ጽ/ቤት ድረስ የመኪና ኪራይና ጫኝ አውራጅ በመሸፈን እስከ ቦረዳ ወረዳ ፋ/ፕ/ጽ/ቤት ማስረከብ አለበት።
6/ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት ቀናት ሲሆን የጨረታው ዝርዝር መረጃ የያዘ ሰነድ ለመግዛት ለወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ 300 / ሦስት መቶ ብር / ብቻ በመክፈል ደረሰኝ በመያዝ ሰነዱን ከፋ/ፕ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ አለበት።
7/ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ፋይናሽያል ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በማድረግ ሙሉ አድራሻ በመግለጽ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሳጥን ክፍት በመሆኑ ተጫራቾች በፋ/ፕ/ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት የሚችሉ መሆኑንና በ16ኛው ቀን በፋ/ፕ/ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥን ይታሸጋል። በዕለቱ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ ፡ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ከወላይታ ሶዶ ከተማ እስከ ቦረዳ ወረዳ ዘፍ ኔከተማ ድረስ ያለው ርቀት 7 ኪሜ
- ከዞኑ ዋና ከተማ አ/ምንጭ እስከ ቦረዳ ዘፍኔ ከተማ ድረስ ያለው ርቀት 94 ኪሜ
- ከአስፋልት እስከ ቦረዳ ወረዳ ዘፍኔ ከተማ ድረስ ያለው ርቀት 24 ኪሜ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-25-13-97-00/ 09-10-44-32-92
በጋሞ ዞን የቦረዳ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት