Addis Zemen (Aug 13, 2026)
በጨረታ ለሚገዙ ዕቃዎች ለተጫራቾች የ1ኛ ዙር
የጨረታ መመሪያ ሰነድ የጨረታ ቁጥር 01/2018
በአገር ውስጥ ለሚፈጸሙ እቃዎችና ተዛማጅ አገልግሎቶች የሚውል የሚገዙ እቃዎች የአላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ አላቂ የት/ት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የእስፖርት እቃዎች የላብራቶሪ እቃዎች 1 የጽዳት እቃዎችና የተለያዩ ቀለሞች፡-
- በመጀመሪያ ደረጃ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የሚችሉት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ያላቸው ወይንም ማቅረብ የሚችሉ ብቻ ናቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሂሳብ የዕቃው አይነት የተመረተበት ዓመተ ምህረት የአገልግሎት ዘመን ማብቂያ የአምራቹ ስም ያካተተ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራቾች በየዘርፉ ንግድ ፈቃድ መኖር አለበት።
- ማንኛውም ተጫራቾች ዋናው የጨረታ ሰነድ ላይ በተጫራቹ የሚሞሉትን በመሙላት እያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም በማኖር ሳይጨምር ሳይቀንስ መመለስ ይኖርበታል።
- የጨረታ ፖስታ ዋናና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት። እነዚህም ሰነዶች የጨረታ አቅራቢው ድርጅት ወይም ህጋዊ ውክልና ባለው አካል መፈረም አለባቸው።
- ተጫራቾች የእቃዎች ናሙና ከየአይነቱ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ የቀረቡት ናሙናዎች
- ለተሸናፊዎች ሲመለሱ የአሸናፈው ተጫራቾች ግን ናሙናዎች አይመለስም አንድ ተብሎ ይቆጠርለታል።
- ግዢ ፈፃሚው አካል አሸናፊ ተጫራቾች በሚመረጡበት ጊዜ የገዛውን እቃ እንደአስፊላጊነቱ እስከ 20% ለመቀነስ ወይም ለመጨመር ይችላል።
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈሎ የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ብቻ።
- የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-9፡00 ይሆናል። ይህ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ አስከ ለ10/አስር/የስራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል፤ በ10ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ወይም ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውን እንዲሁም ስልክ ቁጥራቸውን ማስፈር አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ የማብራሪያ ወይም ማሻሻል አለበት የሚሉ ጥያቄ ካላቸው የጨረታ ሰነዱ የመክፈቻ ጊዜ ሁለት ቀናት እስከሚቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ግዥ ፈፃሚ አካል ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የሰነዱ መሸጫ በሎት ዋጋ 100 መቶ/ ብር ብቻ።
- ማንኛውም ተጫራች ባስገባው ጨረታ ሲፒኦ ማስያዣ ዋጋ ሎት1፡ 10,000 ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት2፣ 10,000 ለፈርኒቸር እቃዎች ሎት3፡2000 ለትምህርት እቃዎች ሎት4፡1000 ለጽዳት እቃዎች፣ ሎት 5፣ 1000 ለተለያዩ ቀለሞች ሎት-6፣ 3000፤ ሌሎች እቃዎች ሎት 7፣ 3000 የእስፖርት እቃዎች፣ ሎት 8፣ 1000 የደንብ ልብስ ሎት 9፣ 4000 ለላቦራቶሪ እቃዎች ሲሆኑ ሰነዱ በራሱ አንድ የጨረታ መመሪያ መሆኑን ተጫራቾች መረዳት ይኖርባቸዋል።
- ከላይ የተዘረዘሩ አንድም ነገር እንኳን የማያሟላ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
- የርክክብ ቦታ በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እቃው ለንብረት ክፍል ካስገባና ጥራቱ ከተረጋገጠ በኋላ ክፍያው ይፈጸማል።
- አድራሻ :- አሰፋ መስማት የተሳናቸው ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቦሌ ክፍስ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ስሙ ኢንስቲትዩት ጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ ነው።
ቦሌ ክፍለ ከተማ አልፋ መስማት የተሳናቸው 2ኛ ደረጃ ልዩ ት/ቤት