የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 13, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎቹን ከ 14/12/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።

ስስሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾ

1. ለተሽከርካሪ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤

2. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እያንዳንዱን ተሽከርካሪ ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤

3. በግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤

4. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካሪ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤

5. ተሽከርካሪውን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በመንግስት ገቢ ይሆናል፤

6. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስቸዋል፤

7. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤

8. ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈለግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤

9. ተጫራቹ ተሽከርካሪውን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤

10. ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ በ11/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቀ/ጽ/ቤት ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፤ ጨረታው በ14/12/2018 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ መኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤

N.B:-

  • አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቀ፤ ተሽከርካሪዎቹን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፣
  • የሻንሲ እና የሞተር ቁጥር የተመታ ተሽከርካሪ ገዝተው መንገድ ትራንስፖርት ሰሌዳ ቁጥር ሲያወጡ መሸጥ እና መለወጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው ሰሌዳ በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት በኩል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *