በቡኖ በደሌ ዞን የሚገኝ የዲዴሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በቡኖ በደሌ ዞን የሚገኝ የዲዴሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 18, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 1/ 2019

በቡኖ በደሌ ዞን የሚገኝ የዲዴሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙት መ/ቤቶቸ (ዲዴሳ ሆስፒታልንና የዲዴሳ ወረዳ ቴ/ሙያ/ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅና የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ( FSRP) የሚያስፈልጉትን ዕቃዎች እነሱም

  • የጽሕፈት መሣሪያዎችና አላቂ የጽዳት ዕቃዎች
  • ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • ፈርኒቸር የቢሮ ዕቃዎች
  • የመኪና ጎማዎች የሞተር ጎማዎችን
  • የመንግሥት ሠራተኞች የደንብ ልብሶችና ጫማዎች
  • ሞተር ሳይክሎችን ሕጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን የመወዳደሪያ መሰፈርቶችን ማሟላት ይጠብቅባችኋል።

1. ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁና ማቅረብ የምትችሉ

2. የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉና 7.5 ለመቁረጥ ፍቃደኛ የሆነ

3. ተወዳዳሪዎች በሀገር ውስጥ ጨረታ ለመወዳዳር የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ወይም ከጉምሩክ ባለሥልጣን ከሀገር ውስጥ ገቢ ወይም ከፌዴራል ሀገር ውሰጥ ገቢ መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው።

4. በአቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ የዕቃው ሞዴል የተመረተበት ዓ.ም የተመረተበት ሀገር ዝርዝር /እስፔስፊኬሽን/ ማቅረብ አለባቸው። ተወዳዳሪዎች በሁሉም የዕቃ ዓይነቶች ላይ ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሙላት አለባቸው።

6. ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ የሕጋዊ ሠነዶቹን ማስረጃዎች ማለት ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ሠነዶች በኦርጂናልና በኮፒ ለየብቻ በማድረግ የዋጋ ማቅረቢያና ሕጋዊ ሠነዶችን በሁለት ሁለት ኮፒ በማዘጋጀት በስም በታሽገ /በኤንቨሎፕ/በማድረግ የሚመለከተውን የድርጅቱን ኃላፊ በማስፈረም ማህተም አድርገውበት በአጠቃላይ በአራት ፖስታ አድርገው በአንድ ላይ ማቅረብ አለባቸው። የጨረታው ሣጥን ከተዘጋ በኋላ የሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

7. ማይክሮዎች ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ካላስያዙ በሚቀርበው ደብዳቤ ብቻ የማንቀበል መሆኑ ይታወቅ።

8. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከብሪያ ብር 50,000 በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም ሲፒኦ ከላይ በተራ ቁጥር 6 ላይ ከተጠቀሰው ሠነድ ጋር ለብቻ በፖስታ በማሸግ ከሕጋዊ ጨረታው ሠነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ሥራ አፈጻጻም የጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

10. ግዥውን የሚያከናውን መ/ቤት ከአሸናፊው ድርጅት ጋር የተፈራረመውን ውል ሳይለውጥ ለመግዛት ትዕዛዝ ከተሰጠው ዕቃ ውስጥ 20% ጨምሮ የመግዛት ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል።

11. ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ከዲዴሳ ወረዳ ገንዘብ ቤት ከቢሮ ቁጥር 4 በብር 1000 የማይመለስ በመክፈል መግዛት ይችላሉ። ሰነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው 02/13/2018 ዓ.ም 6፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ሰነዱን ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በ02/13/2018ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል። ቀኑ የሥራ ሰዓት ላይ ካልዋለ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ተጫራጮች በጨረታዉ መክፈቻ ሥነ-ሰርዓት ላይ ባይገኙም የጨረታዉ ሂደት አይስተጓጎልም።

12. የዕቃው ማስረከቢያ ቦታ ዲዴሳ ወረዳ ገንዘብጽ/ቤት ሆኖ ጠቅላላ የማጓጓዣ የማስጫኛና የማውረጃ ወጪ የሻጭ ግዴታ ይሆናል።

13. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሰዉ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም ።

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፍልም ሆነ ሙሉ በሙለ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

15. ከላይ ከተራቀጥር 1-14 በተጠቀሱት ላይ የማይስማማ ድርጅት መሳተፍ አይችልም።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 12 70 11 05፣ 09 17 22 85 79
የዲዴሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት