Addis Zemen (Aug 18, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
አፈ/ከሳሽ…………………………አፍሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
አፈፃፀም ተከሳሽ……………….ካሳሁን አህመድ
መካከል ባለው የአፃፀም ክርክር ጉዳይ፤በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ሁለገብ እንዱስትሪ ፖርክ ውስጥ በካርታ ቁጥር 30203/03 በሆነ የኢንቨስትመንት ቦታ ላይ ያለ በአፈፃፀም ተከሳሽ ካሳሁን አህመድ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ምርት ማምረት የጀመረ እና የግንባታ ደረጃው 98 ፐርሰንት በላይ የተገነባ የጥራጥሬ ማበጠሪያ ፋብሪካ በግልጽ ጨረታ በመነሻ ዋጋ ብር 37,218,352.08/ ሰላላ ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ አስራ ስምንት ሺህ ሶሶት መቶ አምሳ ሁለት ብር ከዜሮ ስምንት ሳንቲም/ ሆኖ ባለበት ሁኔታ ባህርዳር፤ ከተማ ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ሁለገብ ኢንዱስትሪ ፖርክ ውስጥ በካርታ ቁጥር 30203/03 በሆነ የኢንቨስትመንት ቦታ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሃራጅ በግልጽ ጨረታ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 5፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ በጨረታ እንዲሸጥ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ትዕዛዝ በሰጠው መሰረት የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት 2/ሁለት/ ሰው ታዛቢ በመመደብ የባህርዳር ከተማ 9ኛ ፖሊስ ጽ/ቤትም ፀጥታውን የሚያስከብር አንድ /1/ ሰው በመመደብ የጨረታው ስነ–ስርዓት በአግባቡ እንዲከናወን እንዲደረግ ሆኖ የአብከመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሐራጅ ባይም ጨረታውን በበላይነት በመምራት ጨረታው ይካሄዳል።
ስለሆነም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ማንኛውም ሰው በቦታው በመገኘት ምልከታ አድርጐ ቀርቦ ህጋዊ መታወቂያ በመያዝ መጫረት መሳተፍ የሚቻል እና አሸናፊው እንደታወቀ ያሸነፈበትን ገንዘብ ከተቻለ ሙሉውን ገንዘብ የሚያስይዝ ካልተቻለም አንድ አራተኛውን ወዲያውኑ ማስያዝ የሚችል መሆኑን እንዲያውቁት የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት አዟል።
በአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሐብሔር ዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት