Addis Zemen (Aug 18, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ዲስከበሪ ሞተር ሳይክል ባለ 125 cc ፣ የኤሌክትሪክ ሞተር ቢስክሌት ተጠባባቂ ባትሪ ያለው፤ እና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አሳውጆ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዚህ ጨረታ ስመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተለውን የመወዳደሪያ መስፈርት በማሟላት መወዳደር ይኖርባቸዋል፦
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
2. ግብር ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ከፍያ ንብረት አስ/ር ደጋፍ የሥራ ሂደት እየመጡ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፣
5. ተጫራቹ በባንክ የተረጋገጠ 20,000/ሃያ ሺህ ብር ብቻ የያዘ CPO ወይም የጨረታ ማስከበሪያ ከሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለጨረታው መወዳደሪያ የሚቀርብ CPO በባንክ ማህተምና በባንክ ኃላፊ/ሠራተኞች ፊርማ የተረጋገጠ መሆን አለበት፣
6. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን የዋጋ ማቅረቢያ ሠነዶቻቸውን ኦርጅናልንና የኦርጅናል ኮፒ በፖስታ በማሸግ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ መጨረሻው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዶቻቸውን ማስገባት አለባቸው፡፡ የዕቃውን ጥራት በጥንቃቄ እናያለን፣
7. ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አሥራ አምስት ቀናት/ ከቀኑ 11፡00 ድረስ በሣጥኑ መጨመር አለባቸው፡፡ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሕጋዊ ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሣጥን ይከፈታል፡፡
8. ለጨረታው በዝርዝር ከተጠየቀው ዕቃ ዓይነት ውጪ ለመወዳደር ማቅረብ አይቻልም፤ ለማጭበርበር የሚሞክር ካለ በሕግ ተጠያቂ እናደርጋለን፡፡
9. በጨረታው ሠነድ የተፃፈውን የዕቃ ዓይነት ተጫራቾች በትክክል መሙላት አለባቸው የሚያቀርቧቸው ዋጋ ከቫት ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
10. ያሸነፈ ተጫራች ዕቃውን እስከ መ/ቤቱ ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
11 ፍርድ ቤቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን መለወጥ ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ አድራሻ በስልክ ቁጥር፡- 0939834828 ወይም 0465512100 ደውስው መጠየቅ ይቻላል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት