የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባህርዳር ዲስትሪክት ንብረት በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባህርዳር ዲስትሪክት ንብረት በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 17, 2026)

የመጀመሪያ ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ፤

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባህርዳር ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ለአቶ ተስፋየ አባተ የሰጠው የካፒታል እቃ ተከራዩ የኪራይ ከፍያውን በካፒታል እቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ውሉ መሰረት ሊከፍል ባለመቻሉ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ተረክቦ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

.

የሚሸጠው ንብረት

የሐራጁ መነሻ ዋጋ

ሐራጁ የሚካሄድበት

የንብረቱ ዓይነት

ብዛት

የሚገኝበት አድራሻ

ቀን

ሰዓት

ቦታ

1

Open Type Diesel Generator

(Rated Output: 50-80KVA

Voltage: 400/230V;

Frequency: 50Hz;

Description: 3Ph,

turbocharged, electric starter,

Controller: Digital Automatic

Controller;

Estimated Engine Cylinder: 4- 6 cylinder)

1

እንጅባራ ከተማ

630,619.20

መስከረም 6 ቀን 2019 /

4:00 – 6:00 ሰዓት

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንጅባራ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ

የሐራጁ መመሪያ

  • ተጫራቾች የንብረቱን መነሻ ዋጋ 20% በባንክ ከፍያ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
  • የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ፈቃዱን ካላገኘ የቀረጥ ክፍያው በገዥው ይፈጸማል፡፡
  • ሐራጁ መስከረም 6 ቀን 2019 . ከጠዋቱ 400-600 ሰዓት ይካሄዳል፡፡
  • ሽያጩ የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ነው፡፡
  • አሸናፊው ባሸነፉበት ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል፡፡
  • አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት፡፡ ካልከፈለ ባንኩ የሐራጅ ሽያጩን በመሰረዝ ለማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ በድጋሚ ይካሄዳል፡፡ በድጋሜ ሲሸጥ የሚፈጠረውን የዋጋ ልዩነት ይከፍላል፡፡
  • ጀነሬተሩ አገልገሎት የሰጠ በመሆኑ ጀነሬተሩን የሚመለከቱ ሰነዶች በባንኩ እጅ የማይገኙ ስለሆነ ባንኩ ሰነዶቹን ለአሸናፊው መስጠት አይችልም፡፡
  • ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ የሐራጁ ሽያጭ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ 058-226-27-40

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባህርዳር ዲስትሪክት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *