Addis Zemen (Aug 18, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የውጫሌ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት በወረዳው ለሚገኙ መ/ቤቶች በገጠር የሚገኙ መ/ቤቶች እና ወረዳ ላይ ለሚገኙ ፈንዶቸ አላቂ እቃዎች፤ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኮምፒውተር እና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ የውሀ እና የግንባታ እቃዎች፤ የትምህርት መሳሪያዎች፣ ፈርኒቸሮች፤ የደንብ ልብሶች፤ የስፖርት ትጥቆች፤ የመኪና ጎማ፣ የግሬደር ጎማ፤ የሞተር ጎማ እና ሞተር ሳይክሎች በግልጽጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡–
1. የቫት ተመዝጋቢየሆኑ እና የዘመኑን 2018 /2019 /የመንግስት ግብር የከፈሉ እና የገንዘብ ሚኒስቴር እና ክልል ባወጣው እቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን የሚያቀርቡ፡፡
2.ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ከአ.አ 78ኪ/ሜ ርቀት ላይ በፍቼ መስመር በሚገኘው የውጫሌ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ከቢሮ ቁጥር 08 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ። ጨረታው በዚሁ በ16ተኛው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ4፡00 ሰአት ተዘግቶ በ4፡30 ይከፈታል፤ ሆኖም ተጫራቾች በተጠቀሰው ሰአት ባይገኙም የጨረታ ሣጥኑን መክፈት ይቻላል። 16ተኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ወይም በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይካሄዳል፡፡
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን የእቃዎች ዝርዝር መግለጫ እና የመሸጫ ዋጋ በትክክል በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ ለየብቻበመለየትእና በማሸግ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ የሚመለስ ብር በጥሬ ገንዘብ 20,000/ሀያ ሺሀ/ብር ወይም CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል። CPO/የጨረታ ማስከበሪያው ለብቻው በፖስታ መቅረብ አለበት:: CPO ማቅረብ የማይችል የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከአደራጅ መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና ሲያቀርቡበት ከነበረበት ቦታ ደግሞ ተከታታይ የ2/ሁለት አመት/የ2018እና 2019 የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች ጨረታውን ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በውጫሌ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት እቃ ግምጃ ቤት ሙከ ጡሪ ከተማ ድረስ በማጓጓዝ የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ በመቻል ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
7. መሰሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጫራቾች የእቃውን ሞዴል ወይም ሳምፕል ያሸነፉበትን የእቃ አይነትብቻ ማሳየት ግዴታ አለባቸው።
9. በደንብ ልብስ ውድድር ላይ ሳምፕል ወይም አይነት ያላቀረበ ተወዳዳሪ ከጨረታው ሙሉ በሙሉ ይሰረዛል።፡
10. የጨረታው የመወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በፖስታ /ኤንቬሎፕ/ ታሽጎ ይቀርባል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111 340 657 / 0111 340 019 ደውለው ይጠይቁ፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን የውጫሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
(ሙከጡሪ)