Addis Zemen (Aug 19, 2026)
የኦዲት ሥራ የጨረታ ማስታወቂያ
ስታንድ ፎር ቨልነረብል ድርጅት (ኤስቪኦ) በሕፃናት ተኮርና በሴቶች አቅም ግንባታ ላይ የሚሠራ አትራፊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡
ድርጅቱን የበጎ አድራጎቱን ክንፍ እ.አ.አ የ2026ን እና የሶሻል ኢንተርፕራይዝ የገቢ ማስገኛ ክንፍን እ.ኤ.አ የ2018 የአንድ ዓመት ሂሳብ በተመሠከረለት የኦዲት ድርጅት ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ሥራውን ለማከናወን የሚጠይቁትን የገንዘብ መጠንና ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸውን ጊዜ በመጥቀስ፣ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር (10) የሥራ ቀናት ከታች በተገለጸው አድራሻ መሠረት በፖስታ አሽገው በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡
የኦዲት ድርጅቶቹ የሚከተሉትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡-
ሀ. ኦዲተሩ የሙያ ማረጋገጫ ያለው መሆኑ፣
ለ. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው መሆኑ፣
ሐ. የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆኑ፣
መ. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው መሆኑ፣
ሠ. ከፌዴራል ወይም ከክልል ኦዲተር መሥሪያ ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ ያለው መሆኑ፡፡
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ወደ ዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ላይ ከቴሌ ሕንፃ 300 ሜትር እንዳለፉ በስተቀኝ በኩል የድርጅቱ ታፔላ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0111 261 011 /የቢሮ/ 0927 421 676 / 0911 640 224 /ሞባይል/ መደወል ይቻላል፡፡
ስታንድ ፎር ቨልነረብል ድርጅት (ኤስቪኦ)