የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ለዞን ባለበጀት የመንግስት ሴ/መቤቶች 45 የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ዋስትና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ይዞ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ለዞን ባለበጀት የመንግስት ሴ/መቤቶች 45 የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ዋስትና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ይዞ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል


Be'kur (Aug 17, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ለዞን ባለበጀት የመንግስት ሴ/መቤቶች 45 የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ዋስትና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ይዞ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

3. የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ አሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የጠጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የኢንሹራንስ ዋስትና አገልግሎቶች ዓይነትና የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፍል የጨረታ ሰነዱን ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 08 ማግኘት ይችላሉ፡፡  

7.  ተጫራቾች ለሚወደደሩበት ኢንሹራንስ ዋስትና ሽፋን አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የገንዘብ መጠን ብር 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አን ኮንድሽናል ባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ስም በመክፈል የተከፈለበት ደረሰኝ ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8.  የማወዳደሪያ ሥርዓቱ በሎት ነው፡፡

9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሽገው አዊ ብሔ/አስ/ ገንዘብ መምሪያ ግዥ ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከነሐሴ 11/2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም እስከ  ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዊ ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ግዥ /ን/አስ/ በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 04 ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡15 ይከፈታል፡፡

11. በጨረታው የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች በዞኑ ዋና ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ቢያንስ 1 (አንድ) የኢንሽራንስ ዋስትና ሰጪ ቅርንጫፎች ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13.  ስለ ጨረታው ዝረዝር መረጃ ከፈለጉ አዊ ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ የግዥ ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 227 00 66 /058 227 00 65 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአዊ ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *