Addis Zemen (Aug 20, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሰነድ ቁጥር 008/2018
የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገልግሎት ለምዝገባ ስራ የሚውል ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች ቀርበው እንዲወዳደሩ ይጋብዛሉ።
- ተጫራቾች የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ የንግድ ፋቃዳቸውን ያሳደሱ
- በዘርፉ ለተሰማሩበት ስራ አግባብነት ያለው የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ ቲን ነምበር ያላቸው መሆን አለበት
- ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 200(ሁለት መቶ ብር) ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት ግ/ፋ/ን/አስ የጨረታ ሰነዱን ግዥ መፈጸም ይችላሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 6ኛው ቀን ማለትም ከጠዋቱ 2፡00 ሰአት ፖስታው በሰም ታሽጎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ገቢ ከሆነ በኋላ ተዘግቶ ልክ በዚያው ቀን 2፡30 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0336660883 መደወል ይችላሉ።
የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት