Addis Zemen (Aug 21, 2026)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት አንድ፣ በሎት ሁለት፣ በሎት ሶስት እና በሎት አራት የተዘረዘሩት
- የተለያዩ የሥራ አይነቶች፣
- ጥገና እና ሰርቪስ ሥራዎችን፣
- የሠራተኞችና የተማሪዎች የመዝናኛ ክበብ (የካፍቴሪያ) አገልግሎት ለማሠራት እና
- የተለያዩ ጥገና ሥራዎችን ለማስጠገን
በወጣው ግልጽ ጨረታ ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ የጨረታ አፈፃፀም መመሪያ
- ሎት አንድ፡- ግቢ ውስጥ የሚሠሩ የጥገና ሥራዎች
- ሎት ሁለት፡- የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና ሰርቪስ ሥራዎች
- ሎት ሶስት፡- የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት የተለያዩ ቦታዎች
- ሎት አራት፡-የሠራተኞችና ተማሪዎች የመዝናኛ ክበብ (የካፍቴሪያ) አገልግሎት
እያንዳንዱ ተጫራች የሚከተሉትን ነጥቦች በመረዳት የጨረታ ሰነዳቸውን በዚህ መመሪያ መሰረት አሟልተው እንዲያቀርቡ ያስፈልጋል።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር ወይም ከአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስና ኦኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት የታደሰ፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችዋል።
- የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ቢሮ ቁጥር 34 የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ መረከቢያ ሰዓት ከመድረሱ በፊት መግባት ይኖርበታል።
- ጨረታውን ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ ብር 16,250 ለሎት ሁለት ብር 5,500 ለሎት ሶስት ብር 3,000 እና ለሎት አራት ብር 7,000 CPO በመስሪያ ቤቱ ስም በማሠራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ሎት 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 04 መግዛት ይችላሉ
- በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት ከሥራ ሂደቱ ጋር በሚገባው ውል መሰረት አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ በጠቅላላው ባሸነፈው ዋጋ 10% የሚመለስ በመሥሪያ ቤታችን ስም CPO ማስያዝ ይኖርበታል።
- በዚህ ጨረታ ላይ የሚቀርብ ማንኛውም የመወዳደሪያ ዋጋ ቢያንስ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- የመጫረቻ ሰነድ የማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛ የሥራ ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡ የጨረታው በ11ኛ የሥራ ቀን 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ(ታሽጎ) በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
- የመ/ቤቱ የዕቃ ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ /የገምጋሚ ኮሚቴ ለሥራው የሚያቀርቡትን የዕቃዎቹን ጥራት አይቶ መ/ቤቱ ባወጣው መስፈርት መሰረት ካልቀረበ ጥራት የጎደለው ነው ብሎ ካመነ ዕቃው እንዲመለስ ማድረግ ይችላል።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት /ድርጀቶች ማሸነፍ እንደተገለፀለት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማሰከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ እንደ ምርጫው 2ኛ እና 3ኛ የወጣውን ተወዳዳሪ ሊጋብዝ ይችላል።
- ለውድድር የሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሺያል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ እና ሲፒኦ እያንዳንዱን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅት ፊርማና ማህተም በማድረግ የሚወዳደሩበትን ማቅረብ ይኖርባችዋል።
- ለሎት አንድ ብቻ ግቢ ውስጥ ለሚሠሩ የጥገና ሥራዎች የተቋራጭ ደረጃ GC7/BC 6 እና ከዚያ በላይ የሆነ መሆን ይኖርበታል።
- በመሆኑም በኢትዮጵያ ሕጎች የተደነገጉትን የሚያከብር መሆኑን በማረጋገጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚገኘውን ሙስና ላለመፈፀም ቃል የሚገባበትን ቅፅ በተጫራቹ ተሞልቶና ተፈርሞ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
- የኤሌክትሮኒክስ ጥገና የጨረታው አሸነፊው ድርጅት አስፈላጊ የሆነዉን እቃ እንዲያቀርብ ሲታዘዝ በገበያው ዋጋ መሰረት ማስገባትና መጠገንም ሆነ መሥራት ይኖርበታል።
- ከላይ በተገለፀው መሰረት እያንዳንዱን ጥገና የሚሠራው አሸናፊ ድርጅት ለተጠገነው ዋስትና መስጠት ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 118 35 74 84/+251 118 35 74 76 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
መሥሪያቤቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- ከሆላንድ ኤምባሲ ጀርባ ቀራንዮ መ/ዓለም ቤተ ክርስቲያን
መግቢያ(ቀራንዮ አደባባይ)
የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት