በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም ለወረዳው ለሴክቴር መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም ለወረዳው ለሴክቴር መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 21, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019ዓ.ም ለወረዳው ለሴክቴር መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን ማቴርያልን/ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሰለዚህ አመልካቾች በመንግሥት ግዥ አዋጅና መመሪያ መሠረት፡-

  1. የጽ/መሣሪያ እና አላቂ ዕቃዎች ግዥ CPO ባንክ ጋራንት ወይም ጥሬ ገንዘብ 30,000
  2. የሠራተኞች ደንብ ልብስ CPO ባንክ ጋራንት ወይም ጥሬ ገንዘብ 20,000
  3. ሞተር ሳይክል ግዥ CPO ባንክ ጋራንት ወይም ጥሬ ገንዘብ 30,000
  4. የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች/ፋርኒቸር ግዥ CPO ፣ ባንክ ጋራንት ወይም ጥሬ ገንዘብ 30,000
  5. ግንባታ ዕቃዎች ግዥ CPO ባንክ ጋራንት ወይም ጥሬ ገንዘብ 30000
  6. ኤልክትሮኒክስ ዓይነቶች CPO ባንክ ጋራንት ወይም ጥሬ ገንዘብ 30,000
  7. የተለያዩ የመኪናዎች ጥገና CPO ባንክ ጋራንት ወይም ጥሬ ገንዘብ 40,000

 ስለሆነም በመንግሥት ግዢ አዋጅና ደንብ መመሪያ መሠረት፡

  1. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
  2. የዘመኑ ግብር የተከፈለበት፣
  3. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር /Tin Number/ ፣
  4. ቫት ተመዝጋቢ የሆነ ፣
  5. ከውል ዋጋ ላይ 3% የመንግስት ግብር ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፣
  6.  የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
  7. የአቅራብነት ምዝገባ ምስክር ወርቀት ማቅረብ የሚችል፣
  8. EGP ኦለይን ምዝገባ መረጃ በሀርድ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፤
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረብያ ቦታ ላይ በግልጽ መሙላት አለባቸው።
  10. ተጫራቾች የጨረታውን የሚያቀረቡበትን የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማድረግ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ሆኖ ስማቸውን፤ ፊርማቸውን፤ አድራሻቸውንና የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነትን በትክክል ማሰፈርና በማሸግ በቁ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 ላይ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  11. በጨረታ ሂደት ላይ አሸናፍ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላው ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ 10%ማስያዝ አለበት።
  12. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ሥራ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
  13. ተጫራቾች የሥራ ዝርዝር የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ሥራ ቀናት በቁጫ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናል።
  14. በጨረታ ለመሳተፍ በቅድሚያ በተዘረዘረው መሰረት ጨረታ ዋስትና ሚሆን ቢያንስ ለ60 ቀናት ፀንቶ ሚቆይ በCPO ወይም ባንክጋራንት ወይም ጥሬ ገንዘብ ከላይ በዝርዝር የተገለፁ የጨረታ ማስከበርያ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  15. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው የጨረታው ማብቂያ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡ዐዐ ይሆናል።
  16. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻችው በተገኘበት ይሆናል።
  17. ተጫራቾች ወይም የተጨራቹ ወከል ባለመገኘት ጨረታውን መከፋትን አያስተጓጓልም።
  18. በጨረታ ሂደት አሻናፍ የሆነው ድርጅት ያሸነፉበት ዕቃውን ወደ ቁጫ ወረዳ ፋ/ል/ጽ/ቤት ድረስ ጫኝ አውራጅን ጨምሮ ማድረስ አለበት።
  19. 16ኛው ቀን ሰንበት ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ በጨረታው የተሸለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፍል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046 459 0393 ደውሎ ይጠይቁ።

ሞባይል ቁጥር፡- 09 13 48 34 95/ 09 16 13 80 74

ቁጫ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት