Melekite Dire (Aug 12, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት በ4ቱ ገጠር ከላስተሮች ለሚያስገነባቸው ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ግንባታ የሀገር ውስጥ የወለል ሴራሚክ፣ ቀለም የውሃ፣ ፑቲ፣ ፕራይመሪ፣ ኮንቴክስትራ፣ ቨርኒሽ፣ ጅብሰም የቻክና የቅርፃ ቅርፅ ምርቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመካፈል የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፡-
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊና አግባብነት ያለው የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin
No.) ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የመንግስት መ/ቤቶች በሚፈፅሙት ግዢ
ለመሳተፍ በአቅራቢያዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የጨረታ ማስከበሪያ የ50,000 ብር ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፣ - ተጫራቾች በሙሉ ወይም በከፊል መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የሀገር ውስጥ የሸክላ ምርት፣ የግድግዳ ቀለም የውሃ፣ፕራይመሪ፣ ፑቲ፣
ኮንቴክስትራ፣ የቻክና የቅርፃ ቅርፅ ጅብሰም ናሙና (Sample) ማቅረብ አለባቸው፡፡ - ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶቻቸውን ኦሪጂናልና 1 ኮፒ በማዘጋጀት ለየብቻው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ መ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለብልፅግና ፓርቲ ድ/ዳ/ቅ/ፅ/ቤት ለሃብት አስተዳደር ዘርፍ የሒሳብ ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
- ከብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 በተከታታይ ቀናት ነሐሴ 13/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋት 3፡00 ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው አየር ላይ በዋለ በ15ኛው ቀን ማለትም ነሐሴ 13/2018 ዓ/ም ጠዋት 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ስራ ክፍል ወስጥ ይከፈታል፡፡
- የፓርቲው ቅ/ጽ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኃላ ቅሬታ ያለው አካል በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለቅርንጫፍ ፅህፈትቤቱ ኃላፊ ይቀርባል፡፡
- አሸናፊዎች ያሸነፉትን የግንባታ ግብዓት አሻናፊ ስለመሆኑ የሚገልፅ ደብዳቤ እንደደረሳቸው በ7 ቀን ውስጥ በብልፅግና ፓርቲ ድ/ዳ/ቅ/ፅ/ቤት ለሃብት ለአስተዳደር ዘርፍ ገቢ ማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡