የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ በነጠላና በአፓርትመንት ደረጃ የተዘጋጁ ይዞታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ በነጠላና በአፓርትመንት ደረጃ የተዘጋጁ ይዞታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 21, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን፤ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 (ሀ – ሠ) በተዘረዘረው መሠረት በሐረሪ ከተማ የቀድሞ ደከር /ኹድራ ተራ በሚባል ቦታ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ በነጠላና በአፓርትመንት ደረጃ የተዘጋጁ ይዞታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

የቦታዎቹ ዝርዝር መግለጫ፦

1. ባለ 105 ካ.ሜ ስፋት ያላቸው የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቦታዎች፦ 6 (ስድስት) ፓርሰሎች

2. ባለ 140 ካ.ሜ ስፋት ያላቸው የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቦታዎች፦ 62 (ስልሳ ሁለት) ፓርሰሎች

3. ባለ 150 ካ.ሜ ስፋት ያላቸው የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቦታዎች፦ 2 (ሁለት) ፓርሰሎች

4. የመኖሪያ አፓርትመንት ግንባታ ቦታዎች፦ 6 (ስድስት) ፓርስሎች

የተጫራቾች መመሪያ እና የመወዳደሪያ መስፈርቶች፡

  1. የሰነድ ሽያጭ፦ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተወዳዳሪ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አርብ ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) በመክፈል በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የግዥና ፋይናንስ ሂደት (3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32) ዘወትር በሥራ ቀናትና በሥራ ሰዓት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

2. የሰነድ ማስገቢያ ጊዜ፦ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በመግዛት ለቦታዎች በካሬ ሜትር የሚያቀርቡትን ዋጋ እና የሚከፍሉትን የሊዝ ቅድመ ክፍያ በጨረታ መወዳደሪያ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. የሳጥን መዘጋትና መክፈቻ፦ የጨረታ ሳጥኑ ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ተዘግቶ፣ በሁለተኛው ቀን ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።

4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO)፦ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ቦታ የጠቅላላው የቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 5% (አምስት በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ በጥቅሉ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. የቅድመ ክፍያ መጠን (Minimum Down Payment)፦ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሊዝ ቅድመ ክፍያ መጠን ከአጠቃላይ የሊዝ ዋጋ ከ 15% (አሥራ አምስት ፐርሰንት) ማነስ የለበትም።

6. የግምገማ ነጥብ አሰጣጥ የተጫራቾች አሸናፊነት የሚለየው ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሊዝ ዋጋ 80% (ሰማንያ ፐርሰንት) እና የቅድመ ክፍያ መጠን 20% (ሃያ ፐርሰንት) ጥምር ውጤት ተሰልፎ በሚገኘው ከፍተኛ ነጥብ መሠረት ይሆናል።

7. የCPO ተመላሽ፦ የጨረታው አሸናፊዎች ተለይተው በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በይፋ ከተገለጹ በኋላ በጨረታው ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

8. ማሳሰቢያ፦ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ይፋዊ ድረ-ገፅ https://www.hararilanddev.gov.et  በመግባት ወይም በአካል ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባስሥልጣን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *