በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክ/ከተማ የወረዳ 1 ፋ/ፅ/ቤት የተለያዩ እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክ/ከተማ የወረዳ 1 ፋ/ፅ/ቤት የተለያዩ እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Lessan (Aug 22, 2026)

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር ፅ/ቤት ስር ላሉት ፅ/ቤቶች በ2019 ዓ.ም በጀት አመት የሚያስፈልጋቸውን

  • ሎት 1- የደንብ ልብስ ግዥ – የጨረታ ማስከበሪያ CPO 25000 ብር
  • ሎት 2- የፅህፈት መሳሪያዎች ግዥ – የጨረታ ማስከበሪያ CPO 20000 ብር
  • ሎት 3- የፅዳት እቃዎች ግዥ- የጨረታ ማስከበሪያ CPO 20000 ብር
  • ሎት 4- ልዩ ልዩ እቃዎች ግዥ- የጨረታ ማስከበሪያ CPO 15000 ብር
  • ሎት 5- ደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ CPO 15000 ብር
  • ሎት 6- የመኪና ጎማ እና የተለያዩ እቃዎች ማስከበርያ CPO 30000
  • ሎት 7- የቋሚ እቃ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ CPO 20000
  • ሎት 8 የዲኮር ስራዎች ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ CPO 10000
  • ሎት 9- የትራንስፖርት አገልግሎት የጨረታ ማስከበርያ CPO 10000
  • ሎት 10- የኤሎከትሮኒክስ እና የፈርንቸር ቋሚ እቃ ጥገና ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ CPO 15000
  • ሎት 11- የኤለክትሪክ ጥገና የጨረታ ማስከበርያ CPO 5000
  • ሎት 12- የመስተንግዶ አገልግሎት የጨረታ ማስከበርያ CPO 20000
  • ሎት 13- የህትመት ስራ የጨረታ ማስከበርያ CPO 20000

ብቃት ያላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል በዚህም መሰረት፡-

1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ከላይ በተጠቀሰው አግባብ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

3.ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርከረ አዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት እለት(ቀን) አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር ) በመክፈል በልደታ ክ/ከተማ ወረዳı በሚገኘዉ 2ኛ ፎቅ የመንግስት ግዥ ከፍል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

4.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ለወረዳው ፅ/ቤት 2ኛ ፎቅ ግ/የ/ሂደት ክፍል ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን በ10፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት በወረዳው 4ኛ ፎቅ የመንግስት ግዥ ክፍል ውስጥ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የበዓል/ የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1 ሎት፣ 2 ሎት፣ 3 ሎት፣ 4 ሎት ናሙና ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ሎት 7 ኮምፒተር እንዲሁም ፕሪንተር በስፐስፍከሽን ሌሎች በፎቶ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

7.ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎችና አገልግሎት፤ ለእያንዳንዱ ከቫት ውጭና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8.አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸው እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

9.ተጫራቾች የጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅት ከሆኑ መጫረት የሚችሉት በተደራጁበት ምርት ውጤት ብቻ ሲሆን እንዲሁም ከአደራጃቸው አካል የሚጫረቱበትን እቃ ማቅረብ እደሚችሉ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ:- ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ፋ/ፅ/ቤት ስልክ ቁጥር 011 557 1639

አድራሻ፡- ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር መስከረም ı ት/ቤት ፊት ለፊት፣

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክ/ከተማ የወረዳ 1 ፋ/ፅ/ቤት