በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አንደኛ ዙር ለ2019 ዓ.ም. የበጀት አመት በወረዳው ለሚገኙት መ/ቤቶች፣ የደንብ ልብሶች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቋሚና አላቂ እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸሮች የመኪና እና የሞተር ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አንደኛ ዙር ለ2019 ዓ.ም. የበጀት አመት በወረዳው ለሚገኙት መ/ቤቶች፣ የደንብ ልብሶች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቋሚና አላቂ እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸሮች የመኪና እና የሞተር ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 22, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አንደኛ ዙር ለ2019 ዓ.ም የበጀት አመት በወረዳው ለሚገኙት መ/ቤቶች፡ የደንብ ልብሶች የጽዳት እቃዎች የጽህፈት መሳሪያዎች የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቋሚና አላቂ እቃዎችን፤ የኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸሮች የመኪና እና የሞተር ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የተወዳዳሪዎች መስፈርት

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ግዴታ የተወጡ ስለመሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

3. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተረሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ የቀረቡትን ግዴታዎች አምነው መቀበል አለባቸው።

5. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ መሳተፍ እንደሚችል የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

6. የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ከሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይቻላል።

7. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ተጫራቾች በተገኙበት 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በዛኑ ቀን 4፡ 30 ይከፈታል።

8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተወዳደሩበትን የእቃ ብዛት ተባዝቶ 2% በባንክ በተመሰከረ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ ብቻ መሆን አለባቸው።

9. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት

10. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11. ተጫራቾች በፈለጉትና ማቅረብ በሚችሉት ዕቃዎች ላይ ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡ አሸናፊ ተጫራች ተወዳዳሪ/ የውድድሩ ውጤት ከተነገረበት እስከ 7ኛ ቀን ቀርቦ ውል ካልፈረመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ይወረስበታል።

12. ያሰቀመጥነው ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ መጨመር እና መቀነስም ይቻላል።

13.ተጫራቾች በጨረታ ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎችን ሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ያቀርባሉ።

14. ተጫራቾች ጨረታው ላይ ባይገኙም ጨረታውን መክፈት አያግድም።

15.መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡ ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ ምዕራብ የምትገኘው ሰበታ ከተማ
ለበለጠ መረጃ በስልክ /0912 245 947/011 338 10035
የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት