በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አራብሳ ሣይት 5 ጥላ የጋራ ሕንፃ ቤት ባለቤቶች ህ/ሥ/ ማህበር የኮንደሚኒየም የአጥር ሥራ የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት በዘርፉ ብቃትና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ይጋብዛል – test3.diretenders.com

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አራብሳ ሣይት 5 ጥላ የጋራ ሕንፃ ቤት ባለቤቶች ህ/ሥ/ ማህበር የኮንደሚኒየም የአጥር ሥራ የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት በዘርፉ ብቃትና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ይጋብዛል


Addis Zemen (Aug 27, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ጥ/ የጋ/መ/መ/001/18

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አራብሳ ሣይት 5 ጥላ የጋራ ሕንፃ ቤት ባለቤቶች ህ/ሥ/ ማህበር የኮንደሚኒየም የአጥር ሥራ የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት በዘርፉ ብቃትና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ይጋብዛል።

የሥራው ዝርዝር 455 ሜትር የ Chain Link አጥር ሥራ፣ የኮንክሪት ከርብ ስቶን መሠረት ሥራ፣ የብረት አምድና ቢም ሥራ፣ የበር አምድ፣ የብረት ማጠናከሪያና የመገጣጠሚያ ሥራዎችን ማሠራት ይፈልጋል። 

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

1. በዘርፉ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ያለው፣ የግብር ክሊራንስ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያላቸው።

2. ለሥራው የሚያስፈልጉ የመሥሪያ መሣሪያዎችን፣ የሥራ ቅደም ተከተል work schedule/ እና የሰው ኃይል ዝርዝር ማቅረብ የሚችል።

3. ተመሳሳይ የአጥር ሥራ ልምድ ያለው፤ የሚያስፈልጉ ሕጋዊ ሰነዶችን የሚያቀርብ፤ የሥራውን ጥራትና የተወሰነውን የሥራ ጊዜ ማሟላት የሚችል መሆን አለበት።

4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 /ሃምሣ ሺህ/ በተረጋገጠ ባንክ /CPO/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል አራብሳ ሳይት 5 ጥላ የጋ/ መኖሪያ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰንድ ኦሪጅናልና ኮፒውን ፊርማና ማህተም ያለው በታሸገ ፖስታ ለ7 ተከታታይ ቀናት በተዘጋጀው የመወዳደሪያ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

7. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ8ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 9፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ10፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጥላ ጽ/ቤት ይከፈታል።

8. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት የመዝጊያና የመክፈቻ ቀን ይሆናል።

9. የጨረታ አሸናፊዎች አሸናፊነቱ በጽሑፍ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ በጽ/ቤቱ በመገኘት የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለ ቅድመ ሁኔታ ለግዥ የሚከፈል/Unconditional bank guarantee/ በማስላት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።

10. ሠርቶ የማስረከቢያ ጊዜ 60 ቀንና ከዚያ በታች መሆን አለበት።

11. ተጫራቾች የቴክኒክና ፋይናንሻል ፕሮፖዛሎችን ዋናውና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፤ ሆኖም ግን ለይቶ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።

12. የጨረታ ሰነድን ማባዛት ወይም አሳልፎ መስጠት አይፈቅድም ።

13. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።

14. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።

15. ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. ማሳሰቢያ ውድድሩ የሚካሄደው በነጠላ እና በጠቅላላ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ፡-

አድራሻ፡ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አራብሳ ሣይት በስልክ ቁጥር፤ 09 07 07 50 30 ይደውሉ።
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አራብሳ ሣይት 5 ጥላ የጋራ ሕንፃ ቤት ባለቤቶች ህ/ሥ/ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *