2merkato.com (Aug 27, 2026)
የትንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት የወጣ ጨረታ
ዋን ኤከር ፈንድ በአማራ ክልል የእርሻ ግብአቶችን ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ተሽከርካሪዎችን ለማከራየት ለሚፈልጉ አቅራቢዎች የወጣውን ጨረታ እንዲጫረቱ ይጋብዛል።
- እንደ የእርሻ መሳሪያ እና ዘር ያሉ ግዙፍ መጠን ያላቸውን ግብአቶች ወደ ወረዳ ማዕከል ከተሞች ለማጓጓዝ ስለምንፈልግ የተለያየ መጠን ያላቸውን ተሽከርካሪዎች ማቅረብ የሚችል አቅራቢ ነጋዴ እንፈልጋለን።
- ሁሉም ነጋዴዎች ለሁሉም ተሽከርካሪዎች የንግድ ስራ ፈቃድ፣ ሊብሬ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት እና የታደሰ ቦሎ ሊኖራቸው ይገባል።
- ነጋዴዎች ገንዘብ የሚከፈላቸው በባንክ በኩል ይሆናል። በባንክ ሒሳቡ ላይ ያለው ስም የንግድ ስራ ፈቃድ ከተሰጠው ስም ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት። (ይህ ካልሆነ ነጋዴው የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ አለበት።)
- ነጋዴው መጫረት የሚፈልገው ከ200,000 ብር በላይ በሚጠይቅ ጉዞ ላይ ከሆነ (የረጅም ርቀት ከባድ መኪና ከሆነ) የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- በምትጫረቱበት ጊዜ ለምታጫርቱት ተሽከርካሪ ቀጥተኛ ሃላፊነት ሊኖራችሁ ይገባል። የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ለማግኘት ወደ ተለያየ መስመር የሚደውል ሶስተኛ ወገን እንዲኖር አንፈልግም።
-
- በመሆኑም ወደ ብዙ የጉዞ መስመሮች የሚጫረት ተጫራች የማሸነፍ እድሉ ዝቅተኛ ነው። ይህ ለተሽከርካሪው ቀጥተኛ ሃላፊነት አለመኖሩን ያሳያል።
እባክዎ የሚላክለዎትን የጨረታ ሰነድ በመሙላት ማህተም እና ፊርማ በማስቀመጥ ከሚከተሉት ውስጥ በአንዱ አማራጭ ይላኩ።
- ኢሜይል፦ ethiopia.bidsubmissions@oneacrefund.org
- የቲሌግራም አካውንት፦ @oafbidsubmissions
- የጨረታው የመጨረሻ ቀን:- ነሃሴ 26 2018
ለተጨማሪ መረጃ እና የጉዞ መስመሮች ዝርዝር ለማግኘት በዚህ ስልክ ይደውሉ፡
- 0985654565
- 0984784748
የምናጓጉዝባቸው የጉዞ መስመሮች ዝርዝር ከላይ በተቀመጠው ስልክ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ አንዳንድ መስመሮች ተሽከርካሪው የሚቆምባቸውን እና የሚያራግፍባቸውን ቦታዎች ያካትታሉ። መጫረት ለምትፈልጉት ለእያንዳንዱ የጉዞ መስመር በምታቀርቡት ተሽከርካሪ የጭነት መጠን ትይዩ ላይ መጫረት የምትፈልጉትን ዋጋ ጻፉ። ጨረታውን በቀጥታ ማቅረብ በምትችሉት ተሽከርካሪ መስመር ብቻ ጻፉ።
ማስታወሻ፦ ብዙ አርሶ አደሮች ግብአቶች ከዋን ኤከር ፈንድ በወቅቱ እንዲደርሳቸው ይጠባበቃሉ። በመሆኑም እንዳንዘገይባቸው የሎጂስቲክስ ስራችንን በጥንቃቄ እናቅዳለን። በከፍተኛ ሙያዊ ብቃት የሚያከናውኑንልንን አጋሮች እንፈልጋለን።
ዋን ኤከር ፈንድ ከእያንዳንዱ ማጓጓዝ 2 ሳምንታት ቀደም ብሎ ለሁሉም አቅራቢ ነጋዴዎች የማጓጓዝ እቅድ ይልካል። በኢዝያን ጊዜ ነገዴዎቹ ስለጉዞ አስተያየት መስጠት ወይም ጥያቄ መጠየቅ ይችላሉ። ዋን ኤከር ፈንድ ከማጓጓዝ 2 ቀን ቀደም ብሎ ነጋዴዎቹ በተስማሙት መሰረት ተሽከርካሪዎችን በተሰጣቸው የጉዞ መስመር ላይ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል። ነጋዴው ስለጉዞ ካረጋገጠ በኋላ ተሽከርካሪውን ማቅረብ ካልቻለ ዋን ኤከር ፈንድ ውሉን ሙሉ በሙሉ ሊያቋርጥ ይችላል።
ዋን ኤከር ፈንድ ጥብቅ የሆነ የጸጥታ ፖሊሲ አለው። በመሆኑም ግጭት ባለባቸው መንገዶች ጉዞ እንዲያደርጉ ነጋዴዎችን አይጠይቅም። ነጋዴው መንገዱ የጸጥታ ችግር እንዳለበት ካመነ ከዋን ኤከር ፈንድ ጋር በመነጋገር ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ስምምነት ላይ መድረስ አለበት።